ስፓርት
ዛሬ ምሽት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሦስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ30ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አርሰናል በሜዳው ኢምሬትስ ምስት 3 ሰዓት ከ 45 ላይ ፉልሀምን ያስተናግዳል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ፕሪሚየር ሊጉ ለሀገራት ጨዋታ ሲቋረጥ በመጨረሻ የሊጉ ጨዋታ ቼልሲን ማሸነፉ ይታወሳል።
አርሰናል በ58 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ÷ ተጋጣሚው ፉልሀም በ45 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ ባደረጓቸው ያለፉት አምስት የእርስ በርስ ጨዋታዎች አርሰናል በሁለቱ ሲያሸንፍ÷ ፉልሀም በአንዱ ድል አድርጎ በሁለቱ…
Read More...
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አመራሮችን ያሳተፈው ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገራዊ ለውጡን 7ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ “ትናንት፣ ዛሬንና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ሐሳብ ሲካሄድ የቆየው የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አመራሮች ስፖርታዊ ውድድር ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡
በፍፃሜ ውድድሮቹም፤ በወንዶች የእግር ኳስ ውድድር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማን 4 ለ 0 በሆነ…
የዓለም አቀፍ ጅምናስቲክ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም አቀፍ ጅምናስቲክ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሞሪናሬ ዋታናቤ አዲስ አበባ ገቡ።
የኢትዮጵያ ጅምናስቲክ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ገበያው ታከለ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸል።
ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከባህልና ስፖርት ሚኒስትሮች ጋር እንደሚወያዩና የኢትዮጵያ ጅምናስቲክ ስፖርት…
ክሪስታል ፓላስ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አለፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቀን 9 ሠዓት ከ 15 ላይ በክራቨን ኮቴጅ በተደረገ የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ ፉልሀምን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የክሪስታል ፓላስን የማሸነፊያ ግቦች ኢዜ እና ሳር በመጀመሪያው አጋማሽ ሲያስቆጥሩ፤ ተቀይሮ የገባው ኤዲ ኒኪታህ ቀሪዋን ጎል ከመረብ አሳርፏል፡፡
በዛሬው ጨዋታ ድል…
የኤፍ ኤ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ሲደረጉ ፉልሀም ከክሪስታል ፓላስ እንዲሁም ብራይተን ከኖቲንግሃም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ቀን 9 ሰዓት ከ15 ላይ በማርኮ ሲልቫ የሚመራው ፉልሀም በሜዳው ክራቨን ኮቴጅ ክሪስታል ፓላስን ያስተናግዳል፡፡
ፉልሀም በጥሎ ማለፉ በዚህ የውድድር ዘመን በውጤት ቀውስ ውስጥ…
ቡካዮ ሳካ ከረዥም ጊዜ ጉዳት በኋላ ወደ ልምምድ ተመለሰ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአርሰናሉ ወሳኝ ተጫዋች ቡካዮ ሳካ ከሶስት ወራት ጉዳት በኋላ ወደ ልምምድ መመለሱ ተነግሯል፡፡
ተጫዋቹ ከቡድኑ ጋር ልምምድ መስራቱ የተገለጸ ሲሆን፥ አርሰናል በቻምፒየንስ ሊጉ ከሪያል ማድሪድ ጋር ላለበት ወሳኝ ጨዋታ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡
ቡካዮ ሳካ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በሁሉም ውድድሮች በጎል ተሳትፎ…