ስፓርት
በራስ አል ኬማህ ግማሽ ማራቶን አትሌት እጅጋየሁ ታየ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች በተካሄደው የራስ አል ኬማህ የሴቶች ግማሽ ማራቶን አትሌት እጅጋየሁ ታየ ድል ቀንቷታል፡፡
እጅጋየሁ ግማሽ ማራቶኑን 1 ሰዓት ከአምስት ደቂቃ ከ52 ሴኮንድ በመጨረስ ነው ማሸነፍ የቻለችው፡፡
ኬኒያዊያኖቹ ጁዲ ኬምቦ እና ጀሲካ ቼላንጋት ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን ማጠናቀቃቸውን ከአዘጋጅ ኮሚቴው ድረ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ በወንዶች የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ገመቹ ዲዳ 59 ደቂቃ ከ25 ሴኮንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ…
Read More...
በቻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ምድብ ሪያል ማድሪድ ከማንቼስተር ሲቲ ተደለደለ
አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ድልድል የስፔኑ ሪያል ማድሪድ እና የእንግሊዙ ማንቼስተር ሲቲ ተገናኝተዋል።
የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ድልድል በዛሬው ዕለት ወጥቷል።
የሁለቱ ሃያላን እግር ኳስ ቡድኖች ፍልሚያ የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በኢትሃድ የሚካሄድ…
ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ድቻን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ድቻን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ አብዱ ሳሚዮ እና አማኑኤ ኤርቦ የቅዱስ ጊዮርጊስ ግቦችን አስቆጥረዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም ፈረሰኞቹ ነጥባቸውን ወደ 28 ከፍ…
የሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያው ዙር የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ፍጻሜያቸውን ያገኛሉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሻምፒየንስ ሊግ የመጀመሪያው ዙር የመጨረሻ የምድበ ጨዋታዎች ዛሬ ፍጻሚያቸውን ሲያገኙ ማንቼስተር ሲቲ ከውድድሩ ላለመሰናበት የሚያደርገው ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
ምሽት 5 ሰዓት ላይ ማንቼስተር ሲቲ በኢቲሃድ ስታዲዬም ክለብ ብሩጅን የሚያስተናግድ ሲሆን ከውድድሩ ላለመሰናበት እና የደርሶ መልስ የማጣሪያ ጨዋታን እድል ለማግኘት…
ቤልጂዬማዊው ተጨዋች ኔይንጎላን በአደንዛዥ እጽ ዝውውር ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ዋለ
አዲስ አበባ፣ ጥር 19 ፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቤልጂዬማዊው ተጨዋች ራጃ ኔይንጎላን በአደንዛዥ እጽ ዝውውር ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ፡፡
የ36 ዓመቱ የቀድሞ የኢንተርሚላን እና የሮማ ተጫዋች ራጃ ኔይንጎላን ኮኬይን በመባል የሚታወቀውን አደንዛዥ እጽ ከደቡብ አሜሪካ ወደ አውሮፓ በአንትረፕ ወደብ በኩል ሲያዘዋውር መገኘቱ ተነግሯል፡፡
የአማካኝ ስፍራ ተጨዋቹ…
ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ።
ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ሲዳማ ቡና ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከእረፍት በፊት ናትናኤል ገ/ጊዮርጊስ ባስቆጠራቸው…
ሌስተር ሲቲ ቶተንሃምን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር 11 ሰዓት ላይ ቶተንሃምን ከሌስተር ያገናኘው ጨዋታ በሌስተር ሲቲ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ቶተንሃም በሊጉ ካደረጋቸው 23 ጨዋታዎች 7 ብቻ ያሸነፈ ሲሆን በ13 ጨዋታዎች ተሸንፎ በ24 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ክሪስታል ፓላስ በሜዳው…