ስፓርት
ሌስተር ሲቲ ቶተንሃምን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር 11 ሰዓት ላይ ቶተንሃምን ከሌስተር ያገናኘው ጨዋታ በሌስተር ሲቲ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ቶተንሃም በሊጉ ካደረጋቸው 23 ጨዋታዎች 7 ብቻ ያሸነፈ ሲሆን በ13 ጨዋታዎች ተሸንፎ በ24 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ክሪስታል ፓላስ በሜዳው ከብሬንትፎርድ ጋር ተጫውቶ 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡
Read More...
አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ የኦሳካ ማራቶን ውድድርን አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ በጃፓን ኦሳካ በተካሄደ የሴቶች ማራቶን ውድድር አሸናፊ ሆነች።
አትሌቷ ርቀቱን ለመጨረስ 2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ59 ሴኮንድ የፈጀባት ሲሆን ባለፈው ዓመት በቦታው ውድድሩን ስታሸነፍ ካስመዘገበችው 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ51 ሰኮንድ ጋር ሲነጻጸር በ2 ደቂቃ ከ51 ሰኮንዶች ዘግይታለች።
አትሌት…
ማንቸስተር ሲቲ ቼልሲን 3 ለ 1 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ23ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ማንቸስተር ሲቲ ቼልሲን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
ምሽት 2፡30 ላይ በተካሄደው ጨዋታ ቼልሲ በኖኒ ማዱኬ ጎል ሲመራ ቢቆይም ባለሜዳው ማንቸስተር ሲቲ በኧርሊንግ ሃላንድ፣ በተከላካዩ ዮሽኮ ግቫርዲዮል እና በፊል ፎደን ጎሎች ማሸነፍ ችሏል።…
አትሌት ማርታ የ3000 ሜትር ክብረ ወሰን በመስበር አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በካዛኪስታን ዋና ከተማ አስታን በተካሄደ ከ18 ዓመት በታች የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አትሌት ማርታ አለማየሁ ክብረ ወሰን በመስበር አሸንፋለች።
የ16 ዓመቷ አትሌት ማርታ ርቀቱን ለመጨረስ 8 ደቂቃ ከ39 ሰኮንድ ከ80 ማይክሮ ሰኮንድ የሆነ ጊዜ የወሰደባት ሲሆን ከዚህ በፊት ፈጣኑ ሰዓት 8 ደቂቃ…
ሊቨርፑል እና አርሰናል ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተካሄደ የ23ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ሊቨርፑል እና አርሰናል ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል።
ሊቨርፑል ኤፕስዊች ታውንን 4 ለ 1 በማሸነፍ መሪነቱን ባጠናከረበት ጨዋታ የማሸነፊያ ግቦችን ዶሚኒክ ስቦዝላይ፣ መሀመድ ሳላህ እንዲሁም ኮዲ ጋክፖ ሁለት ግቦች ሲያስቆጥሩ…
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሰባት አመታት ተቋርጦ የነበረው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።
በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ(ፕ/ር) ÷የስፖርት ፌስቲቫሉ መዘጋጀቱ ጥቅሙ የጎላ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በአምስት የስፖርት…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ከቼልሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ23ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢቲሃድ ስታዲየም ላይ ማንቼስተር ሲቲ ከቼልሲ ዛሬ ምሽት የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
ምሽት 2፡30 ላይ በሚደረገው ጨዋታ ሩበን ዲያዝ እና ጀረሚ ዶኩ በጉዳት የማይሰለፉ ሲሆን÷አዲስ ፈራሚዎቹ ኦማር ማርሙሽ፣ ቪቶር ሬይስ እና አብዱኮዲረ ኩሳኖቭ በማንቼስተር ሲቲ የቡድን…