ስፓርት
መቻል ስሑል ሽረን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ13ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስሑል ሽረ በመቻል 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡
የመቻልን ግቦች ሽመልስ በቀለ በ24ኛው እንዲሁም ግሩም ሀጎስ በ39ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
የስሑል ሽረን የማስተዛዘኛ ግብ ደግሞ አስቻለው ታመነ በ53ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ አስቆጥሯል፡፡
የዛሬው የመጨረሻ የጨዋታ መርሐ-ግብር መካሄዱን ሲቀጥል 12 ሠዓት ላይ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይጫወታሉ፡፡
Read More...
መቐለ 70 እንደርታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ13ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቐለ 70 እንደርታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 ረትቷል፡፡
የማሸነፊያዋን ግብም አዎት ኪዳኔ በ82ኛው ደቂቃ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡
በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው የ13ኛ ሣምንት የዕለቱ መርሐ-ግብር ሲቀጥል÷ አዳማ ከተማ ከቅዱስ…
ዌስትሃም ዩናይትድ አሰልጣኙን አሰናበተ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንግሊዙ ክለብ ዌስትሃም ዩናይትድ አሰልጣኝ ጁለን ሎፕቴጌን ከስድስት ወራት ቆይታ በኋላ ከኃላፊነታቸው ማሰናበቱ ተሰምቷል፡፡
ስፔናዊው የ58 አመት አሰልጣኝ የለንደኑን ክለብ በአሰልጣኝነት የተረከቡት ከዴቪድ ሞይስ ስንብት በኋላ ነበር፡፡
መዶሻዎቹ በፕሪሚየር ሊጉ በሰባት ነጥብ ብቻ…
ባህርዳር ከተማ ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህርዳር ከተማ ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ባህርዳር ከተማ በጄሮም ፍሊፕ ብቸኛ ጎል ሀዋሳ ከተማን 1 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም የጣና ሞገዶቹ ነጥባቸውን ወደ 22 ከፍ በማድረግ…
ኢትዮጵያ መድን ስሑል ሽረን አሸንፏል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ12ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ መድን ስሑል ሽረን 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡
መሐመድ አበራ፣ ረመዳን የሱፍ እና መስፍን ዋሼ የኢትዮጵያ መድን ጎሎችን ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
የስሑል ሽረን ግብ ያስቆጠረው ደግሞ አሌክስ ኪታታ ነው፡፡
በአዳማ ሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው የዛሬ…
አዳማ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ12ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 0 ረትቷል፡፡
በአዳማ ሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ÷ የአዳማ ከተማን ጎሎች አሜ መሐመድ፣ ነቢል ኑሪ እና ኤሊያስ ለገሠ አስቆጥረዋል፡፡
በሌላ የጨዋታ መርሐ-ግብር በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመቐለ 70…
ሊቨርፑል ታሪካዊ ተቀናቃኙ ማንቸስተር ዩናይትድን ዛሬ ይገጥማል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር መሪው ሊቨርፑል 14ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ማንቸስተር ዩናይትድን ዛሬ ምሽት በሜዳው አንፊልድ ሮድ ያስተናግዳል፡፡
ሊጉ በፈረንጆቹ 1992/93 የውድድር ዓመት በአዲስ መልክ ከተዋቀረ ጀምሮ 65 ጊዜ ተገናኝተው ማንቸስተር ዩናይትዶች 29 ጊዜ ሲያሸንፉ በአንፃሩ…