Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የኤልክላሲኮ የፍፃሜ ጨዋታ በሳዑዲ አረቢያ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በስፔን ሱፐር ካፕ ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና (ኤልክላሲኮ) የሚያደርጉት የፍጻሜ ጨዋታ  ይጠበቃል፡፡ ጨዋታው በሳዑዲ ኪንግ አብዱላህ ስፖርት ሲቲ ስታዲየም ምሽት  4 ሰዓት ይደረጋል፡፡ በሱፐር ካፑ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ባርሴሎና አትሌትክ ቢልባኦን እንዲሁም ሪያል ማድሪድ ሪያል ሞዮርካን በማሸነፍ ለዛሬው የፍጻሜ ጨዋታ ደርሰዋል፡፡ በኤልክላሲኮ የመጀመሪያ ዙር የላሊጋ ጨዋታ ባርሴሎና ሪያል ማድሪድን 4 ለ 0 ማሸነፉ አይዘነጋም፡፡
Read More...

በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እስከ 10 ደረጃን በመያዝ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ ድል አስመዘገቡ። ከማለዳው 11 ሰዓት ጀምሮ በዱባይ በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያውያኑ የተሰጣቸውን ቅድሚያ ግምት አሳክተዋል። በዚህም በሁለቱም ጾታ ከአንደኛ እስከ አስረኛ ድረስ ያለውን ደረጃ በመያዝ በፍጹም የበላይነት…

ሀድያ ሆሳዕና እና ፋሲል ከነማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀድያ ሆሳዕና እና ፋሲል ከነማ አንድ አቻ ተለያዩ፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ብሩክ በየነ ለሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ማርቲን ኪዛ ለፋሲል ከነማ ግቦቹን አስቆትረዋል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ ሀድያ ሆሳዕና የሊጉን መሪነት ለመቻል…

መቻል ስሑል ሽረን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ13ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስሑል ሽረ በመቻል 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡ የመቻልን ግቦች ሽመልስ በቀለ በ24ኛው እንዲሁም ግሩም ሀጎስ በ39ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ የስሑል ሽረን የማስተዛዘኛ ግብ ደግሞ አስቻለው ታመነ በ53ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ አስቆጥሯል፡፡ የዛሬው የመጨረሻ የጨዋታ መርሐ-ግብር…

መቐለ 70 እንደርታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ13ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቐለ 70 እንደርታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 ረትቷል፡፡ የማሸነፊያዋን ግብም አዎት ኪዳኔ በ82ኛው ደቂቃ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡ በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው የ13ኛ ሣምንት የዕለቱ መርሐ-ግብር ሲቀጥል÷ አዳማ ከተማ ከቅዱስ…

ዌስትሃም ዩናይትድ አሰልጣኙን አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንግሊዙ ክለብ ዌስትሃም ዩናይትድ አሰልጣኝ ጁለን ሎፕቴጌን ከስድስት ወራት ቆይታ በኋላ ከኃላፊነታቸው ማሰናበቱ ተሰምቷል፡፡ ስፔናዊው የ58 አመት አሰልጣኝ የለንደኑን ክለብ በአሰልጣኝነት የተረከቡት ከዴቪድ ሞይስ ስንብት በኋላ ነበር፡፡ መዶሻዎቹ በፕሪሚየር ሊጉ በሰባት ነጥብ ብቻ…

ባህርዳር ከተማ ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህርዳር ከተማ ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ባህርዳር ከተማ በጄሮም ፍሊፕ ብቸኛ ጎል ሀዋሳ ከተማን 1 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም የጣና ሞገዶቹ ነጥባቸውን ወደ 22 ከፍ በማድረግ…