Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ዋሊያዎቹ በደርሶ መልስ በሱዳን አቻቸው ተሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን በሱዳን 2 ለ 1 ተሸነፈ፡፡ ጨዋታው ዛሬ 11 ሠዓት ላይ በሊቢያ ቤንጋዚ ቤኒና ማርትየርስ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡ ዋሊያዎቹ በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ 2 ለ 0 ዛሬ ደግሞ 2 ለ1 መሸነፋቸውን ተከትሎ በደርሶ መልስ ድምር ውጤት 4 ለ 1 ተረትተው ከውድድሩ ተሰናብተዋል፡፡
Read More...

ዋሊያዎቹ የቻን የመልስ ጨዋታቸውን ከሱዳን አቻቸው ጋር ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ከሱዳን አቻው ጋር ያደርጋል፡፡ የሁለቱ ቡድኖች የቻን የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ ጨዋታ 11 ሠዓት ላይ በሊቢያ ቤንጋዚ ቤኒና ማርትየርስ ስታዲየም ይደረጋል። ብሔራዊ ቡድኑ በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በሱዳን 2 ለ 0 መሸነፉ…

የማንቼስትር ዩናይትድ ስታዲየም ኦልድትራፎርድ የአይጥ መንጋ አስቸግሮታል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ ሜዳ የሆነው ኦልድትራፎርድ በአይጥ መንጋ መቸገሩ ተሰምቷል፡፡ የንጽህና ተቆጣጣሪዎች በቅርቡ ባደረጉት ምልከታ÷ስታዲየሙ አይጥ በብዛት እንደመሸገበት መረዳታቸውንና ለቡድኑ የምግብ ንጽህና የሁለት ኮከብ ምዘና (ሬቲንግ) እንደሰጡት ተገልጿል። በዚህም ለቡድኑ የምግብ ንጽህና ከአራት ኮከብ ወደ ሁለት…

ቡካዮ ሳካ ለበርካታ ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እንግሊዛዊው የአርሴናል ክንፍ ተጫዋች ቡካዮ ሳካ ለበርካታ ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ገልጿል፡፡ ተጫዋቹ አርሴናል ክርስታል ፓላስን 5 ለ 1 ባሸነፈበት ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ በጡንቻ መሸማቀቅ ጉዳት ከሜዳ መውጣቱ ይታወሳል፡፡ የቡድኑ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በሰጠው መግለጫ ÷ ቡካዮ ሳካን…

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን  በሱዳን አቻው ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ ውድድር (ቻን) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሱዳን አቻው 2ለ 0  ተሸንፏል፡፡ የሁለቱ ቡድኖች የቻን የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ ቀን 11 ሰዓት በሊቢያ ቤንጋዚ ቤኒና ማርትየርስ ስታዲየም ተደርጓል፡፡ በጨዋታውም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን  በሱዳን አቻው…

ማንቼስተር ዩናይትድ ሲሸነፍ ቼልሲ ነጥብ ጣለ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መረሐ ግብር ኦልድትራፎርድ ላይ ቦርንሞውዝን ያስተናገደው ማንቼስተር ዩናይትድ 3 ለ 0 ሲሸነፍ  ቼልሲ በኤቨርተን ነጥብ ጥሏል፡፡ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ለቦርንሞውዝ የማሸነፊያ ግቦችን ዲያን ሁጅሰን፣ ክሉቨርት እና ሴሜኞ አስቆጥረዋል፡፡…

አትሌት መሠረት ደፋር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሆና ተመረጠች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መርጠዋል። በዚህም 14 ወንድ እና 12 ሴት ለዕጩነት የቀረቡ ሲሆን÷ አትሌት መሰረት ደፋር፣ወ/ሮ ሳራ ሀሰን፣ ወ/ሮ አበባ የሱፍ፣ ኤፍራህ መሀመድ(ዶ/ር)፣ አቶ ቢንያም ምሩፅ፣ አቶ አድማሱ ሳጅን፣ ጌቱ ገረመው(ኢ/ር)…