Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ማንቼስተር ሲቲ ዛሬም ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አስቶንቪላ በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘውን ማንቼስተር ሲቲን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡ በቪላ ፓርክ በተደረገው ጨዋታ የነገሡት አስቶንቪላዎች÷ ጆን ዱራን በ16ኛው እንዲሁም ሞርጋን ሮጀርስ በ65ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ግቦች ተጋጣሚያቸውን ረትተዋል፡፡ የማንቼስተር ሲቲን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ጎል ደግሞ ፊል ፎደን በ93ኛው ደቂቃ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡ እንደአጀማመራቸው መሆን እየተሳናቸው ያሉት ውኃሰማያውዮቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስኬታማ መንገድ…
Read More...

በሊጉ የበዓል ሰሞን መርሐ-ግብር ማንቼስተር ሲቲ ከአስቶንቪላ፤ክሪስታል ፓላስ ከአርሰናል ዛሬ ይጫወታሉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ማንቼስተር ሲቲ ከአስቶንቪላ እንዲሁም ክሪስታል ፓላስ ከአርሴናል ዛሬ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ። በከፍተኛ የውጤት ማጣት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንቼስተር ሲቲ ወደቪላ ፓርክ ተጉዞ ከቀኑ 9:30 ላይ ከአስቶን ቪላ ጋር በሚያከናውነው ጨዋታ ከባድ ፈተና እንደሚጠብቀው…

አትሌት ድርቤ  በግራንድ ስላም ትራክ ውድድር ለመሳተፍ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ድርቤ ወልተጂ የግል የውድድር መድረክ በሆነው የግራንድ ስላም ትራክ  ውድድር ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የኮንትራት ስምምነት ፈርማለች፡፡ በስምምነቱ መሰረት በ1 ሺህ 500 ሜትር  ርቀት ላይ በመወዳደር የምትታወቀው አትሌት ድርቤ በ2025 በአሜሪካ በሚደረገው የግራንድ ስላም ትራክ ውድድር ላይ ትሳተፋለች፡፡…

ለማህበራዊ ሚዲያ ጥቃት ለተጋለጡ 25 አትሌቶች የኤአይ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም አትሌቲክስ 25 የተለያዩ ሀገራት አትሌቶች ራሳቸውን ከማህበራዊ ሚዲያ ጥቃት እንዲከላከሉ የሚያስችል የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ (ኤአይ) ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ ተቋሙ ባደረገው የአራት ዓመታት ጥናት አትሌቶቹ ለከፋ የማህበራዊ ሚዲያ ጥቃት ተጋላጭ መሆናቸው ተገልጿል። በመሆኑም የማህበራዊ ሚዲያ ጥቃት…

ሪያል ማድሪድ የኢንተርኮንቲኔንታል ካፕ ዋንጫን አነሳ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ የ2024 የፊፋ ኢንተርኮንቲኔንታል ካፕ ዋንጫን አንስቷል፡፡ ማድሪድ ዋንጫውን ለማንሳት የበቃው ከሜክሲኮው ክለብ ፓቹካ ጋር ያደረገውን የፍፃሜ ጨዋታ 3 ለ 0 በመርታት ነው፡፡ ኪሊያን ምባፔ፣ ሮድሪጎ እና ቪኒሺየስ ጁኒየር ደግሞ ግቦቹን ከመረብ ማሳረፋቸውን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡

ቪኒሺየስ ጁኒየር የፊፋ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)ብራዚላዊው የሪያል ማድረዱ ተጫዋች ቪኒሽየስ ጁኒየር የ2024 የፊፋ የወንዶች ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመረጠ። ተጫዋቹ በውድድር ዓመቱ ለሪያል ማድሪድ የስፔን ላሊጋንና የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ እንዲያሸንፍ ከፍተኛ አስተፅኦ አድርጓል። ተጫዋቹ ለቡድኑ 24 ጎሎችን አስቆጥሮ 11 ለግብ የሚሆኑ ኳሶች አመቻችቶ አቀብሏል።…

ሙድሪክ በጊዜያዊነት ከዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ውድድሮች ታገደ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዩክሬናዊው የቼልሲ የክንፍ መስመር ተጫዋች ሚካዬሎ ሙድሪክ በጊዜያዊነት ከዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ውድድሮች መታገዱ ተረጋግጧል፡፡ ውሳኔው የተላለፈው ተጫዋቹ ያልተፈቀደ አበረታች ቅመም ተጠቅሟል በሚል ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ተከትሎ ነው፡፡ ቼልሲ እና ተጫዋቹ ሙድሪክም የእንግሊዝ እግር ኳስ ማኅበር እያከናወነ…