ስፓርት
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኖርዊች ሲቲ የመጀመሪያው ወራጅ ቡድን ሆኗል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ35ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜና እሁድ ተደርገዋል።
ቅዳሜ በተደረጉ ጨዋታዎች በዌስትሃም ዩናይትድ የተሸነፈው ኖርዊች ሲቲ ወደ ሻምፒየን ሺፑ መውረዱን ያረጋገጠ የመጀመሪያው ቡድን ሆኗል።
ጨዋታውን የመውረድ ስጋት ያለበት ዌስትሃም ዩናይትድ 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በሌሎች ጨዋታዎች ሊቨርፑል ከበርንሌይ አንድ አቻ ሲለያይ ቼልሲ ደግሞ በሼፊልድ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
ቅዳሜ ምሽት ላይ ከብራይተን የተጫወተው ማንቼስተር ሲቲ 5 ለ 0 በሆነ ውጤት…
Read More...
በፕሪሚየር ሊጉ ሊቨርፑል ሲሸነፍ በላ ሊጋ ሪያል ማድሪድ መሪነቱን አጠናክሯል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በስፔን ላ ሊጋ ትናንት በተደረገ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ መሪነቱን ያጠናከረበትን ውጤት አስመዝግቧል።
ማድሪድ ከጌታፌ ተጫውቶ 1 ለ 0 በማሸነፍ ከተከታዩ ባርሴሎና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት 4 አድርሶታል።
ባርሴሎና ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ተጫውቶ ሁለት አቻ መለያየቱ ይታወሳል።
ውጤቱን ተከትሎም ሪያል ማድሪድ በ74…
ሊቨርፑል ከ30 ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋገጠ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሊቨርፑል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋገጠ፡፡
የአንፊልዱ ክለብ ትናንት ምሽት ተከታዩ ማንቼስተር ሲቲ በቼልሲ መሸነፉን ተከትሎ ከ30 አመት በኋላ ሻምፒዮንነቱን አውጇል፡፡
የክለቡ ደጋፊዎችና ተጫዋቾች ከረጅም አመታት በኋላ የተገኘውን ድል አክብረውታል፡፡
አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ሁኔታዎች ሲመቻቹ…
በፕሪሚየር ሊጉ ቶተንሃም በላ ሊጋው ደግሞ ባርሴሎና ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ ፣ሰኔ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትናንት ምሽት በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች የሃገር ውስጥ ውድድሮች ተካሄደዋል።
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገው ቶተንሃም ሆትስፐርስ ድል ቀንቶታል።
ቀደም ብሎ በተደረገ ጨዋታ በሜዳው ብራይተንን ያስተናገደው ሌሲስተር ሲቲ ጨዋታውን ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ጨርሷል።
በጨዋታው ብራይተኖች ያገኙት የፍጹም…
ለበጎ አድራጎት ድጋፍ ማሰባሰቢያ የሜዳ ቴኒስ ላይ የተሳተፈው ዲሚትሮቭ የኮሮና ቫይረስ ተገኘበት
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ታዋቂው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ግሪጎር ዲሚትሮቭ ለበጎ አድራጎት ድጋፍ ማሰባሰቢያ በተዘጋጀ ጨዋታ ላይ ከተሳተፈ በኋላ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት ተነገረ።
በወንዶች የሜዳ ቴኒስ ቀዳሚ በሆነው ኖቫክ ጃኮቪች አስተባባሪነት በተዘጋጀው የበጎ አድራጎት ድጋፍ ማሰባሰቢያ ላይ ከተሳተፈ በኋላ ነው ቡልጋራዊው የሜዳ ቴኒስ…
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ለፋሲልና ለባህር ዳር ከነማ እግር ኳስ ክለቦች ለእያንዳንዳቸው የ3 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ለፋሲልና ለባህር ዳር ከነማ እግር ኳስ ክለቦች ለእያንዳንዳቸው የ3 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።
የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ሀላፊ አቶ አገኘው ተሻገረ የባህር ዳርና ፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ክለቦች በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክልሉን ወክለው የሚጫወቱ በመሆኑ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም አቻ ተለያይተዋል
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ትናንት ምሽት ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል።
ቀደም ብሎ በተካሄደ ጨዋታ ከሜዳው ውጭ ከኖርዊች ሲቲ የተጫወተው ሳውዝሃምፕተን 3 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።
ዳኒ ኢንግስ፣ አርምስትሮንግ እና ሬድሞንድ የድል ጎሎችን አስቆጥረዋል።
ምሽት 4 ሰአት ከ15 በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ቶተንሃም ሆትስፐርስ…