ስፓርት
በፕሪሚየር ሊጉ አዳማ ከተማ ወልቂጤ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ አንድ ጨዋታ ተደርጓል።
እንግዳው ወልቂጤ ከተማ ከአዳማ ከተማ ጋር ተጨውተው አዳማ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ፕሪሚየር ሊጉ ነገም ሲቀጥል ፋሲል ከነማ ከሜዳው ውጭ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ይጫወታል።
እንዲሁም መቐለ 70 እንደርታ በሜዳው ባህር ዳር ከተማን ያስተናግዳል።
ሰበታ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ወላይታ ዲቻ ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ሃዋሳ ከተማ ከሃዲያ ሆሳዕና፣ ጅማ አባጅፋር ከኢትዮጵያ ቡና እና ስሑል ሽረ…
Read More...
ሎዛ በማልታ ሊግ ባደረገቻቸው 12 ጨዋታዎች 30 ጎሎች አስቆጥራለች #ፋና ስፖርት
https://www.youtube.com/watch?v=rjKk3R4nQHw
አርሰናል ከማንቼስተር ሲቲ ዛሬ ምሽት ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ተራዘመ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከማንቼስተር ሲቲ ዛሬ ምሽት ሊያደርጉት የነበረው ተጠባቂ ጨዋታ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተራዘመ።
ጨዋታው የተራዘመው የግሪኩ እግር ኳስ ክለብ ኦሊምፒያኮስ ባለቤት ኢቫንጄሎስ ማሪናኪስ በትናንትናው ዕለት በተደረገላቸው ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ተከትሎ ነው።…
አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ 24 ተጫዋቾችን ጠሩ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ለ2021ዱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 24 ተጫዋቾችን ጠርቷል።
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ዋልያዎቹ ከኒጀር ብሔራዊ ቡድን ጋር ለሚያደርጉት የደርሶ መልስ ጨዋታ ነው።
ተጫዋቾቹ ከ13 የኘሪሚየር ሊጉ ክለቦች የተመረጡ ሲሆን፥ ለግብፁ አል መካስ እግር ኳስ ክለብ የሚጫወተው ሽመልስ በቀለ…
4ኛው የቶኪዮ ኦሊምፒክ የኢትዮጵያ ችቦ በመቐለ ተለኮሰ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ 4ኛው ዙር የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ቡድን ችቦ የመለኮስ ስነስርዓት በመቐለ ከተማ ተካሄደ፡፡
በስነ ስርዓቱ ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን የቶኪዮ 2020 ብሄራዊ የዝግጅት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳን ጨምሮ የትግራይ…
በሎስ አንጀለስ ማራቶን አትሌት ባየልኝ አሸናፊ ሆነ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት በሎስ አንጀለስ በተደረገ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ባየልኝ ተሻገር አሸናፊ ሆኗል።
አትሌት ባየልኝ ርቀቱን 2 ሰዓት ከ8 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ በመግባት አሸናፊ ሆኗል።
ኬንያውያኑ ጆን ላጋት እና ዊልሰን ቼቤት ደግሞ ሁለተኛ እና ሶስተኛ…