Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከተማ አቻ ተለያየ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ብቸኛ ጨዋታ ዛሬ ተካሂዷል። የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል። ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ፋሲል ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ መሸነፋቸው ይታወሳል። ፕሪሚየር ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ28 ነጥብ ሲመራ ፋሲል ከነማ በ26፣ መቐለ 70 እንደርታ በ25 ነጥቦች ይከተላሉ። ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ደግሞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ…
Read More...

ባምላክ ተሰማ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታን ይመራል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው የመሃል ዳኛ ባምላክ ተሰማ የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግን ይመራል። ኢትዮጵያዊው የመሐል ዳኛ ቲፒ ማዜምቤ በሜዳው ከሞሮኮው ራጃ ካዛብላንካ ጋር የሚያደርጉትን የቻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ የሚመራ ይሆናል። የመጀመሪያው ጨዋታ በመጭው አርብ ካዛብላንካ ላይ የሚደረግ ሲሆን የመልሱ ጨዋታ ደግሞ ሉሙምባሺ ላይ…

የቀድሞው የካፍ ዋና ፀሀፊ አምር ፋህሚ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ዋና ፀሀፊ አምር ፋህሚ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ግብፃዊው አምር ፋህሚ በካንሰር ህመም ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው፥ በ36 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ፋህሚ ከፈረንጆቹ 2017 እስከ 2019 ድረስ የካፍ ዋና ፀሃፊ ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል።…

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና፣ ሀዋሳ ከተማ እና ባህርዳር ከነማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ቡና፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ባህርዳር ከነማ እና ድሬዳዋ ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል። ወላይታ ድቻን በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች…

በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና ሰበታ ከተማ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ብቸኛ ጨዋታ ዛሬ ተካሂዷል። ሰበታ ከተማን በሜዳው ያስተናገደው  ሲዳማ ቡና ሰበታ ከተማን  1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የሲዳማን ብቸኛ የማሸነፊያ ጎልም  ይገዙ ቦጋለ በ56ተኛው ደቂቃ ማስቆጠር ችሏል። የሊጉ በርከት ያሉ ጨዋታዎችም ነገ የሚካሄዱ ይሆናል።