ስፓርት
አትሌት አባብል የሻነህ በግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ሰበረች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ራስ አል ከሂማህ በተካሄደ የሴቶች ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አባብል የሻነህ የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር አሸነፈች።
አትሌት አባብል በፈረንጆቹ 2017 ኬንያዊቷ አትሌት ጆይስሊን ጄፕኮስጊ በቫሌንሺያ የያዘችውን ክብረ ወሰን በ20 ሰከንድ በማሻሻል አሸንፋለች።
በውድድሩ አትሌት አባብል የሻነህ ርቀቱን 1 ሰዓት፣ ከ4 ደቂቃ፣ ከ31 ሰከንድ በመግባት አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን በማስመዝገብ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቃለች።
በውድድሩ ኬንያውያን አትሌቶች…
Read More...
በፈረንሳይ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፈረንሳይ ሌቪን ትናንት ምሽት በተካሄደ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።
ኢትዮጵያውያኑ በ1 ሺህ 500 ሜትር በወንድ እና ሴት እንዲሁም በ3 ሺህ ሜትር ወንዶች በበላይነት ማጠናቀቅ ችለዋል።
በዚህ መሰረት በወንዶች 3 ሺህ ሜትር አትሌት ጌትነት ዋለ 7 ደቂቃ፣ ከ32 ሰከንድ፣…
የቻን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)በካሜሮን አዘጋጅነት የሚካሄደው የቻን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ፡፡
ከሁለት ወራት በኃላ ለሚጀመረው የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያዉን ያለፉ ሀገራት የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል::
በዚህም በምድብ አንድ ካሜሮን፣ ማሊ፣ቡሪኪና ፋሶ እና ዚምባቡዌ ሲደለደሉ በምድብ ሁለት ሊቢያ ፣ዲሚክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ኮንጎ…
በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና ሲያሸንፍ ኢትዮጵያ ቡና አቻ ተለያይቷል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ዛሬ ተከናውኗል።
በሜዳው ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው ወልቂጤ ከተማ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ሰበታ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ተገናኝተው ጨዋታውን ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት አጠናቀዋል።
ውጤቱን ተከትሎም…
በፕሪሚየር ሊጉ የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት በክልል ከተማዎች በዛሬው ዕለት 5 ጨዋታዎች ተካሂደዋል።
በሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።
በዚህም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሜዳው ውጭ አንድ ነጥብ በማግኘት በ27 ነጥብ የአንደኝነት ደረጃውን ሲያስጠብቅ በተመሳሳይ ፋሲል…
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን የመጀመሪያው ችቦ በይፋ ተለኮሰ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን የመጀመሪያው ችቦ በአዲስ አበባ በይፋ ተለኮሰ።
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴም የኦሎምፒክ ቡድኑ የቶክዮ 2020 የመጀመሪያውን ችቦ በይፋ ለኩሰዋል።
በዚህም ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት “እኛ ኢትዮጵያውያን በተባባረ አንድነትና ህብረት ወደ ላቀ ብልፅግና እንደርሳለን፤ ኢትዮጵያ ብዙ…
በፕሪሚየር ሊጉ መቐለ 70 እንደርታ ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ብቸኛ ጨዋታ ዛሬ ተካሂዷል።
ሀዋሳ ከተማን በትግራይ ስታዲየም ያስተናገደው መቐለ 70 እንደርታ 5 ለ1 በሆነ ሰፊ ልዩነት አሸንፏል።
የመቐለ 70 እንደርታን የማሸነፊያ ግቦች ኦኪኪ አፎላቢ፣ ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ እና ቢያድግልኝ ኤልያስ አስቆጥረዋል።
የሀዋሳ ከተማን ብቸኛ…