Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪምየር ሊጉ ሰበታ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል። ሰበታ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ ሰበታ ከተማ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የሰበታ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ፍፁም ገብረማርያም እና አዲስ ተስፋዬ ሲያስቆጥሩ፥የሃዋሳ ከተማን ብቸኛ ግብ ደግሞ መስፍን ታፈሰ አስቆጥሯል። እንዲሁም መቐለ 70 እንደርታን ሶዶ ከተማ ላይ ያስተናገደው ወላይታ ድቻ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። የወላይታ ድቻን…
Read More...

36ኛው የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር ነገ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 37ኛው የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር ነገ በጃንሜዳ ይካሄዳል። በውድድሩ አምስት ክልሎች፣ ሁለት የከተማ አስተዳደሮች፣ 37 ክለቦች እና የማሰልጠኛ ተቋማት የሚሳተፉ ይሆናል። 6 ኪሎ ሜትር ወጣት ሴቶች ፤ በ10 ኪሎ ሜትር አዋቂ ሴቶች፣ በወንዶች 8 ኪሎ ሜትር ወጣት ወንዶች፣ በ10 ኪሎ ሜትር አዋቂ…

ጠ/ሚ ዐቢይ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅት ከተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበጃፓን ቶኪዮ ለሚካሄደው ኦሊምፒክ የሚደረጉ ዝግጅቶችን ለማስተባበር ከተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ። በውይይቱ ወቅት ኮሚቴው ለቶኪዮ ኦሊምፒክ እያደረገ ያለውን ዝግጅት በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል። በውድድሩ ከተሳትፎ ባለፈ አትሌቶች በድል እንዲመለሱ የማገዝ አላማ እንዳለው መግለጹን…

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያውን እሁድ ያደርጋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ለህንዱ የታዳጊዎች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን የፊታችን እሁድ ያከናውናል። ብሄራዊ ቡድኑ በአሰልጣኝ ሳሙኤል አበራ እየተመራ ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ በባህር ዳር ልምምዱን እያከናወነ ይገኛል። ጨዋታው እሁድ 9 ሰዓት በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስቴዲየም…

በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 15 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ተከታትለው በመግባት አሸናፊ ሆነዋል። በወንዶች አትሌት ኦሊቃ አዱኛ 2 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቋል። ኬንያዊው አትሌት ኤሪክ ኪፕሮኖ 2ኛ ደረጃን ሲይዝ ከ3ኛ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትለው…

አሰልጣኝ ሁሴን ሺቦ የአመቱ የአፍሪካ ምርጥ አትሌቲክስ አሰልጣኝ ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን በ2019 በአትሌቲክሱ ዘርፍ የአመቱን ምርጦች ይፋ አድርጓል። በአሰልጣኞች ዘርፍ ኢትዮጵያዊው አሰልጣኝ ሁሴን ሺቦ የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ሆነው ተመርጠዋል። ከዚህ ባለፈም አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ እና አትሌት ለሜቻ ግርማ ደግሞ በሁለቱም ጾታዎች የአመቱ ምርጥ ወጣት አትሌት ዘርፍ…

ኢትዮጵያ ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጋና እና ደቡብ አፍሪካ ጋር ተደልድላለች

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለ2022 የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ድልድል ተጋጣሚዎች ተለይተዋል። የማጣሪያ የምድብ ድልድሉ ትናንት ይፋ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ በምድብ 7 ተደልድላለች። በምድቡ ጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባብዌ የኢትዮጵያ ተጋጣሚዎች ሆነዋል። በማጣሪያው የየምድቦቹ አሸናፊዎች በዕጣ ድልድል እርስ…