ስፓርት
ሮናልዶ ከፕሬዚዳንትነት ምርጫ እራሱን አገለለ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀድሞው የብራዚል እና ሪያል ማድሪድ አንጋፋ ተጫዋች ሮናልዶ ሉዊስ ናዛሪዮ ዲሊማ ከሀገሩ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነት ምርጫ እራሱን ማግለሉን ይፋ አደረገ፡፡
የ48 ዓመቱ የቀድሞ ዝነኛ ተጫዋች፤ የወቅቱን የብራዚል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኤድናልዶ ሮድሪጌዝ ለመተካት በሚደረገው ምርጫ በዕጩነት እንደሚቀርብ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጂ ከሀገሪቱ ክልሎች የሚጠበቀውን ያህል ድጋፍ አለማግኘቱን ገልጾ፤ ከውድድሩ እራሱን ማግለሉን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አሳውቋል፡፡…
Read More...
ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ድሬዳዋ ከተማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 22ኛ ሣምንት የጨዋታ መርሐ-ግብር የተገናኙት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ድሬዳዋ ከተማ አቻ ተለያይተዋል፡፡
በአዳማ ሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ፤ ክለቦቹ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡
ፋሲል ከነማ መቻልን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ22ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ መቻልን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በጨዋታው ለፋሲል ከነማ ጌታነህ ከበደ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር÷ ቀሪዎቹን ደግሞ ቢኒያም ጌታቸው እና ምኞት ደበበ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
መቻልን ከሽንፈት ያልታደጉትን ሁለት ግቦች አቤል ነጋሽ እና ፊሊሞን…
ፓትሪስ ሞትሴፔ የካፍ ፕሬዚዳንት በመሆን በድጋሚ ተመረጡ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፓትሪስ ሞትሴፔ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት ሆነው ለሁለተኛ ጊዜ ያለምንም ተቀናቃኝ ተመርጠዋል።
ደቡብ አፍሪካዊው የ63 ዓመቱ የወቅቱ የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ በድጋሚ መመረጣቸውን ተከትሎ እስከ 2029 ድረስ ካፍን በፕሬዚዳንትነት ይመራሉ።
የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ)…
የአርባምንጭ ስታዲየም ግንባታ በ4 ነጥብ 32 ቢሊየን ብር ወጪ እየተከናወነ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአርባምንጭ ስታዲየም ግንባታ በ4 ነጥብ 32 ቢሊየን ብር ወጪ እየተከናወነ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ኦላዶ ኦሎ ገለጹ፡፡
ግንባታውን በሁለት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ ውል መገባቱን አውስተዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በፈረንጆቹ ሐምሌ 28 ቀን 2024 መጀመሩን ገልጸው፤ እስከ አሳለፍነው የካቲት…
በሻምፒየንስ ሊጉ አትሌቲኮ ማድሪድ ከሪያል ማድሪድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አትሌቲኮ ማድሪድ ከሪያል ማድሪድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
የሻምፒየንስ ሊጉ የ16ቱ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ቀጥለው ሲደረጉ፤ አትሌቲኮ ማድሪድ በሜዳው የከተማ ተቀናቃኙን ሪያል ማድሪድን ምሽት 5 ሠዓት ላይ ያስተናግዳል።
በሁሉም ውድድር ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት…
ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ22ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መሐ-ግብር ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊያ ግቦች አለን ካይዋ እና አቡበከር ሳኒ ሲያስቆጥሩ፤ ንግድ ባንክን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ግብ ኪቲካ ጅማ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን ያሳካው…