ስፓርት
ክሪስታል ፓላስ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አለፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቀን 9 ሠዓት ከ 15 ላይ በክራቨን ኮቴጅ በተደረገ የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ ፉልሀምን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የክሪስታል ፓላስን የማሸነፊያ ግቦች ኢዜ እና ሳር በመጀመሪያው አጋማሽ ሲያስቆጥሩ፤ ተቀይሮ የገባው ኤዲ ኒኪታህ ቀሪዋን ጎል ከመረብ አሳርፏል፡፡
በዛሬው ጨዋታ ድል የቀናው ክሪስታል ፓላስ በሁሉም ውድድር ባደረጋቸው ያለፉት ስድስት ጨዋታዎች አልተሸነፈም፡፡
የኤፍ ኤ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ሲቀጥል ብራይተን በሜዳው ኖቲንግሀም…
Read More...
የኤፍ ኤ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ሲደረጉ ፉልሀም ከክሪስታል ፓላስ እንዲሁም ብራይተን ከኖቲንግሃም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ቀን 9 ሰዓት ከ15 ላይ በማርኮ ሲልቫ የሚመራው ፉልሀም በሜዳው ክራቨን ኮቴጅ ክሪስታል ፓላስን ያስተናግዳል፡፡
ፉልሀም በጥሎ ማለፉ በዚህ የውድድር ዘመን በውጤት ቀውስ ውስጥ…
ቡካዮ ሳካ ከረዥም ጊዜ ጉዳት በኋላ ወደ ልምምድ ተመለሰ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአርሰናሉ ወሳኝ ተጫዋች ቡካዮ ሳካ ከሶስት ወራት ጉዳት በኋላ ወደ ልምምድ መመለሱ ተነግሯል፡፡
ተጫዋቹ ከቡድኑ ጋር ልምምድ መስራቱ የተገለጸ ሲሆን፥ አርሰናል በቻምፒየንስ ሊጉ ከሪያል ማድሪድ ጋር ላለበት ወሳኝ ጨዋታ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡
ቡካዮ ሳካ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በሁሉም ውድድሮች በጎል ተሳትፎ…
አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የደጋፊዎች ድምጽ አሸናፊ ሆነች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሰሞኑን በተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በ1 ሺህ 500 ሜትር ርቅት የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቷ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ የደጋፊዎች ድምጽ አሸናፊ ሆናለች፡፡
የዓለም አትሌቲክስ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ ባጋራው መረጃ፤ ከደጋፊዎች ባሰባሰበው ድምጽ መሠረት አትሌት ጉዳፍ ማሸነፏን አስታውቋል፡፡
በዓለም የቤት ውስጥ…
አርጀንቲና አራት ጨዋታ እየቀራት ወደ ዓለም ዋንጫ አለፈች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ አሜሪካ ሀገራት የ2026 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከብራዚል ጋር ጨዋታዋን ያደረገችው አርጀንቲና 4 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።
የአርጀንቲናን የማሸነፊያ ግቦች ዩሊያን አልቫሬዝ፣ ኢንዞ ፈርናንዴዝ፣ አሌክሲስ ማክ አሊስተር እና ጁሊያኖ ሲሞን ሲያስቆጥሩ፤ ብራዚልን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛዋን ግብ ማቲያስ ኩንሀ…
ሴፕ ብላተር እና ሚሼል ፕላቲኒ ከቀረበባቸው ክስ በድጋሚ በነፃ ተሰናበቱ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀድሞ የፊፋ ፕሬዚዳንት ሴፕ ብላተር እና የቀድሞ የዩኤፋ ፕሬዚዳንት ሚሼል ፕላቲኒ ከቀረበባቸው በፊፋ የፋይናንሺያል የስነ ምግባር ጥሰት ክስ በነፃ መሰናበታቸው ተገልጿል።
ሁለቱ የቀድሞ የእግር ኳስ ከፍተኛ ኃላፊዎች በፈረንጆቹ 2011 ላይ ፈፅመዋል ከተባሉበት የ2 ሚሊየን ዶላር ማጭበርበር ወንጀል ክስ በስዊዘርላንድ ፍርድ…