ስፓርት
ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ረፋድ በተደረገው ጨዋታ ሀብታሙ ታደሰ ለሲዳማ ቡና እንዲሁም ዳዋ ሁጤሳ (በፍፁም ቅጣት ምት) የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ግቦችን አስቆጥረዋል፡፡
የ20ኛ ሳምንት መርሃ ግብሮች ከሰዓት ቀጥሎ ሲካሄዱ ቀን 9 ሰዓት ስሑል ሽረ ከኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም ምሽት 12 ሰዓት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከአዳማ ከተማ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
Read More...
ሉሲዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የዑጋንዳ አቻውን በመለያ ምት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ዙር ማለፉን አረጋግጧል፡፡
ሉሲዎቹ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በካምፓላ ባደረጉበት ወቅት 2 ለ 0 መሸነፋቸው ይታወሳል፡፡
ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው የመልስ ጨዋታ፤ ሉሲዎቹ አረጋሽ ካልሳ እና እፀገነት ግርማ…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት ሊቨርፑል ከኒውካስል ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በዋንጫ ፉክክሩ ላይ ወሳኝነት ያላቸው ተጠባቂ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይከናወናሉ።
የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ምሽት 5 ሰዓት ከ15 የቀጣይ ዓመት የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎን ለማግኘት የሚፋለመውን ኒውካስል ዩናይትድ በአንፊልድ ያስተናግዳል።
ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎ ምሽት 4:30 ላይ…
መቻል 21 ሚሊየን ብር እንዲሁም ሲዳማ ቡና 18 ሚሊየን ብር ተቀጡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ተሳታፊ የሆነው መቻል እግር ኳስ ክለብ የ21 ሚሊየን ብር እንዲሁም ሲዳማ ቡና የ18 ሚሊየን ብር ቅጣት የተላለፈባቸው መሆኑን የሊጉ የፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡
ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ÷በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የክለቦች የክፍያ ሥርዓት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1/2016 አንቀጽ…
አትሌት ሰለሞን ባረጋ የሲቪያ ማራቶንን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ሰለሞን ባረጋ በስፔን ሲቪያ በተካሄደው የማራቶን ውድድር አሸንፏል፡፡
አትሌት ሰለሞን 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ በመግባት ነው የማራቶን ውድድሩን ያሸነፈው፡፡
አትሌት ሰለሞን ባረጋ የማራቶን ውድድሩን ለመጀመሪያ ጊዜ ማድረጉንም የኢትዮጵያ አቲሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ…
ማንቼስተር ሲቲ ከሊቨርፑል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ከሊቨርፑል የሚያደርጉት ፍልሚያ በጉጉት ይጠበቃል፡፡
ጨዋታው ምሽት 1 ሰዓት ከ30 በኤቲሃድ ስታዲየም ይደረጋል፡፡
አርሰናል በትናንትናው እለት በዌስትሃም ዩናይትድ መሸነፉን ተከትሎ ሊጉን በ8 ነጥብ ልዩነት እየመራ የሚገኘው ሊቨርፑል የዛሬውን…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል በዌስትሃም ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሜዳው ዌስትሃም ዩናይትድን ያስተናገደው አርሰናል 1 ለ ዐ ተሸንፏል።
የዌስትሃምን የማሸነፊያ ጎል ጃሮድ ቦውን በ45ኛ ደቂቃ ሲያስቆጥር፥ ከአርሰናል በኩል ወጣቱ ተከላካይ ሊውስ ስኬሊ በሁለተኛው አጋማሽ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
በሌሎች የ12 ሰዓት ጨዋታዎች፣ ብራይተን…