ስፓርት
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ድልድል ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ድልድል በስዊዘርላንድ ናዮን ይፋ ተደርጓል።
በዚህ መሰረትም አርሰናል ከኔዘርላንድሱ ፒ ኤስ ቪ አይንድሆቨን እንዲሁም ሊቨርፑል ከፒ ኤስ ጂ ጋር ተደልድለዋል።
በተጨማሪም ባየርን ሙኒክ ከባየር ሊቨርኩሰን፣ ክለብ ብሩገ ከአስቶንቪላ፣ ቦሩሺያ ዶርትመንድ ከሊል፣ አትሌቲኮ ማድሪድ ከሪያል ማድሪድ፣ ፌይኖርድ ከኢንተር ሚላን እና ቤኔፊካ ከባርሴሎና መደልደላቸውን የሊጉ መረጃ ያመላክታል፡
Read More...
በሻምፒየንስ ሊግ ሪያል ማድሪድ ከማንቼስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ሲከናወኑ ሳንቲያጎ ቤርናባው ላይ ሪያል ማድሪድ ከማንቼስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል፡፡
ኤቲሃድ ስታዲየም ላይ በተደረገው የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ሪያል ማድሪድ 3 ለ 2 ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ምሽት በውድድሩ ለመቆየት የሚደረገው የሁለቱ ኃያላን…
ቀነኒሳ በቀለ በ2025 የለንደን ማራቶን እንደሚሳተፍ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት 2025 በሚካሄደው የለንደን ማራቶን እንደሚሳተፍ አስታውቋል፡፡
በ40 ዓመት ዕድሜ ላይ የሚገኘው አትሌት ቀነኒሳ የለንደን ማራቶን የመጨረሻው ዓለም አቀፋዊ ውድድር ሊሆን እንደሚችል ተመላክቷል፡፡
በለንደን ማራቶን በድጋሚ እንደሚሳተፍ በማህበራዊ ትስስር ገጹ…
አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ በኦርሌን የ1 ሺህ 500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ በኦርሌን የ1 ሺህ 500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር የራሷን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈች
አትሌቷ ውድድሩን 3 ደቂቃ ከ53 ሴኮንድ ከ92 ማይክሮ ሴኮንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ በራሷ ተይዞ የቆውን ክብረ ወሰን በ83 ማይክሮ ሰከንድ አሻሽላለች፡፡
አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬን በመከተል አትሌት ብርቄ…
ሊቨርፑል መሪነቱን የሚያጠናክር ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር አንፊልድ ላይ ዎልቭስን ያስተናገደው ሊቨርፐል 2 ለ 1 በማሸነፍ ነጥቡን 60 በማድረስ መሪነቱን አጠናክሯል።
ሊቨርፑል በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ባደረገው በዚህ ጨዋታ በደረጃ ሰንጠረዡ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ያሰፋበትን…
አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በካስትሎ 10 ኪሎ ሜትር ውድድር አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በስፔን ካስትሎ በተካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር የወንዶች ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸንፏል፡፡
አትሌት ዮሚፍ ርቀቱን 26 ደቂቃ ከ3 ሰከንድ በመግባት ነው በቀዳሚነት ማጠናቀቅ የቻለው፡፡
በውድድሩ ዮሚፍ የራሱን የ10 ኪሎ ሜትር እና የቦታውን ምርጥ ሰዓት ማስመዝገቡን የአዘጋጅ ኮሚቴው መረጃ ያመላክታል፡፡
የሰሜን ኮሪያው መሪ ሶስት የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች በሀገራቸው እንዳይታዩ አገዱ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ቶተንሃም ሆትስፐር፣ ዎልቭስ እና ብረንትፎርድ በሀገሪቱ ቴሌቪዥን እንዳይታዩ ማገዳቸው ተገለፀ፡፡
ኪም ጆንግ ኡን ትዕዛዙን የሰጡት በሶስት ክለቦች የሚጫዎቱ የደቡብ ኮሪያ ተጫዋቾችን የሰሜን ኮሪያ ዜጎች እንዳይመለከቷቸው ለማድረግ ነው ተብላል፡፡
የቶተንሃም አምበል እና አጥቂ ሰን ሁንግ…