ስፓርት
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ከቼልሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ23ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢቲሃድ ስታዲየም ላይ ማንቼስተር ሲቲ ከቼልሲ ዛሬ ምሽት የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
ምሽት 2፡30 ላይ በሚደረገው ጨዋታ ሩበን ዲያዝ እና ጀረሚ ዶኩ በጉዳት የማይሰለፉ ሲሆን÷አዲስ ፈራሚዎቹ ኦማር ማርሙሽ፣ ቪቶር ሬይስ እና አብዱኮዲረ ኩሳኖቭ በማንቼስተር ሲቲ የቡድን ስብስብ ውስጥ እንደሚኖሩ አሰልጣኝ ፔፕ ጓርዲዮላ አስታውቀዋል፡፡
በቼልሲ በኩል ሌቪ ኮልዊል እና ኤንዞ ፈርናንዴዝ ከጉዳት መልስ ለጨዋታው ብቁ መሆናቸው ተነግሯል፡፡…
Read More...
ዎከር ወደ ኤሲሚላን …
አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እንግሊዛዊው የማንቼስተር ሲቲ የክንፍ ተከላካይ ካይል ዎከር በውሰት ውል ወደ ጣሊያኑ ክለብ ኤሲ ሚላን ለመዘዋወር ከስምምነት መድረሱ ተሰምቷል፡፡
በውሉ መሰረት ኤሲሚላን የ34 ዓመቱን ተጫዋች በቋሚነት የማስፈርም መብት ማግኘቱ ተነግሯል፡፡
የውኃ ሰማያዊዮቹ አምበል ዝውውሩን ለማጠናቀቅ እና የሕክምና ምርመራውን ለማድረግ…
ሐዋሳ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሐዋሳ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቀዋል፡፡
ቀን 9:00 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ለሐዋሳ ከተማ ናትናኤል ዘለቀ እንዲሁም ለወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ…
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ 7ኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ምሽት ላይ ሲደረጉ ቤኔፊካ ከባርሴሎና እንዲሁም አትሌቲኮ ማድሪድ ከባየርሊቨርጉሰን የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
ምሽት 2 ከ45 ላይ ቤርጋሞ ላይ አታላንታ ከስትሩም ግራዝ እንዲሁም ሞናኮ ከአስቶንቪላ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ምሽት 5 ሠዓት ላይ ደግሞ አትሌቲኮ…
ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው በብራይተን ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 22ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ በብራይተን 3 ለ1 ተሸንፏል፡፡
የብራይተንን የማሸነፊያ ግቦች ሚንቴህ ፣ ሚቶማ እና ሩተር ከመረብ ሲያሳርፉ÷የዩናይትድን ብቸኛ ግብ ደግሞ ፈርናንዴዝ አስቆጥሯል።
በተመሳሳይ ኖቲንግሃም ፎረስት ሳውዝሃምፕተንን እንዲሁም ኤቨርተን ቶተንሃምን 3 ለ 2…
ወላይታ ድቻና ሲዳማ ቡና አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና አቻ ተለያይተዋል፡፡
ቡድኖቹ ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡
የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል መቐለ 70 እንደርታ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ምሽት12…
አርሰናል እና አስቶንቪላ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኤምሬትስ ስታዲየም የተደረገው የአርሰናል እና አስቶንቪላ ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡
ይህን ጨዋታ አርሰናል ማርቲኔሊ በ35ኛው እና ሀቨርትዝ በ55ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ግቦች ሲመራ ቆይቷል፡፡
ይሁን እንጂ ቴሌማንስ በ60ኛው እንዲሁም ዋትኪንስ በ68ኛው ግብ ማስቆጠራቸው ተከትሎ የመድፈኞቹ መሪነት ከ13…