ስፓርት
ሊድስ ዩናይትድ ከ16 አመታት በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ተመለሰ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሊድስ ዩናይትድ ከ16 አመታት በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለሱን አረጋግጧል።
የዮርክሻየሩ ክለብ ከረጅም አመታት በኋላ ከሻምፒዮንሺፑ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ዳግም ተመልሷል።
ትናንት ምሽት ተከታዩ ዌስትብሮምዊች አልቢዮን በሃድስፊልድ ታዎን 2 ለ 1 ተሸንፏል።
ይህን ተከትሎም በአርጀንቲናዊው ማርሴሎ ቢዬልሳ የሚመራው ክለብ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ዳግም መመለሱ ተረጋግጧል።
ሊድስ ዩናይትድ በ44 ጨዋታዎች 87 ነጥብ የሰበሰበ ሲሆን የሻምፒዮን ሺፑ አሸናፊ ለመሆን ከቀሪ ሁለት ጨዋታዎቹ አንድ…
Read More...
ሪያል ማድሪድ የስፔን ላ ሊጋ አሸናፊ መሆኑን አረጋገጠ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሪያል ማድሪድ የዘንድሮው የስፔን ላ ሊጋ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
ትናንት ምሽት የላ ሊጋው 37ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡
በሜዳው ቪያሪያልን ያስተናገደው ሪያል ማድሪድ 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
ይህን ተከትሎም ላ ሊጋውን ለ34ኛ ጊዜ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
በሌላ በኩል ከኦሳሱና የተጫወተው…
ማንቼስተር ሲቲ በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ተጥሎበት የነበረው እገዳ ተነሳለት
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ ማንቼስተር ሲቲ በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ተጥሎበት የነበረው እገዳ ተነሳለት።
ክለቡ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበርን የገንዘብ አስተዳደር (የፋይናንሺያል ፌር ፕሌይን) ባለማክበር እንዲሁም ከፈረንጆቹ 2012 እስከ 2016 ከስፖንሰር ሺፕ አግንቸዋለሁ በሚል ለአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ያቀረበው…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኖርዊች ሲቲ የመጀመሪያው ወራጅ ቡድን ሆኗል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ35ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜና እሁድ ተደርገዋል።
ቅዳሜ በተደረጉ ጨዋታዎች በዌስትሃም ዩናይትድ የተሸነፈው ኖርዊች ሲቲ ወደ ሻምፒየን ሺፑ መውረዱን ያረጋገጠ የመጀመሪያው ቡድን ሆኗል።
ጨዋታውን የመውረድ ስጋት ያለበት ዌስትሃም ዩናይትድ 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በሌሎች ጨዋታዎች…
በፕሪሚየር ሊጉ ሊቨርፑል ሲሸነፍ በላ ሊጋ ሪያል ማድሪድ መሪነቱን አጠናክሯል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በስፔን ላ ሊጋ ትናንት በተደረገ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ መሪነቱን ያጠናከረበትን ውጤት አስመዝግቧል።
ማድሪድ ከጌታፌ ተጫውቶ 1 ለ 0 በማሸነፍ ከተከታዩ ባርሴሎና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት 4 አድርሶታል።
ባርሴሎና ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ተጫውቶ ሁለት አቻ መለያየቱ ይታወሳል።
ውጤቱን ተከትሎም ሪያል ማድሪድ በ74…
ሊቨርፑል ከ30 ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋገጠ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሊቨርፑል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋገጠ፡፡
የአንፊልዱ ክለብ ትናንት ምሽት ተከታዩ ማንቼስተር ሲቲ በቼልሲ መሸነፉን ተከትሎ ከ30 አመት በኋላ ሻምፒዮንነቱን አውጇል፡፡
የክለቡ ደጋፊዎችና ተጫዋቾች ከረጅም አመታት በኋላ የተገኘውን ድል አክብረውታል፡፡
አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ሁኔታዎች ሲመቻቹ…
በፕሪሚየር ሊጉ ቶተንሃም በላ ሊጋው ደግሞ ባርሴሎና ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ ፣ሰኔ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትናንት ምሽት በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች የሃገር ውስጥ ውድድሮች ተካሄደዋል።
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገው ቶተንሃም ሆትስፐርስ ድል ቀንቶታል።
ቀደም ብሎ በተደረገ ጨዋታ በሜዳው ብራይተንን ያስተናገደው ሌሲስተር ሲቲ ጨዋታውን ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ጨርሷል።
በጨዋታው ብራይተኖች ያገኙት የፍጹም…