Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የሴኔጋልና የሊቨርፑሉ አጥቂ ሳዲዮ ማኔ የአፍሪካ የዓመቱ ኮኮብ ተጫዋች ሆነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን እና የሊቨርፑሉ አጥቂ ሳዲዮ ማኔ በአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) የአፍሪካ የዓመቱ ኮኮብ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ፡፡ ሳዲዮ ማኔ የዓመቱ ኮኮብ ተጫዋችነት ሽልማትን ያገኘነው የቡድን አጋሩን ሞሃመድ ሳላህ እና የአልጀሪያና የማንቼስተር ሲቲውን የመስመር ተጫዋች ሪያድ ማህሬዝን አስከትሎ ነው። የ27 ዓመቱ የሊቨርፑል አጥቂ በ2018/2019 በሁሉም ውድድሮች 30 ጎሎችኝ በማስቆጠር ቀያዮች የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን እንዲያነሱ አስችሏል፡፡ እንዲሁም ሊቨርፑል…
Read More...

በቻይና በተካሄደ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱ ጾታዎች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል። በቻይና በተደረገው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያኑ ሲያሸንፉ በሴቶች ምድብ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል። በውድድሩ በወንዶች አትሌት ብርሃን ንባባው ርቀቱን በ2 ሰዓት ከ8 ደቂቃ ከ16 ሰከንድ…

በፕሪምየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ መቐለ 70 እንደርታን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዛሬ በተካሄደው 6 ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ  መቐለ 70 እንደርታን አሸንፏል። መቐለ 70 እንደርታን በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ  2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። የቅዱስ ጊርጊስን የማሸነፊያ ግቦች ሳላህዲን ሰዒድ እና አቤል ያለው ሲያስቆጥሩ፥ አሸናፊ ሀፍቱ…

6ኛው የብዙሃን ስፖርት በመስቀል አደባባይ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ስድስተኛው ዙር የብዙሃን ስፖርት መርሃ-ግብር ዛሬ በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል። አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግን ባህል ያደረገ ከተማ እና ህብረተሰብ መፍጠርን ዓላማ ባደረገው በዚህ ሁነት በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። የዛሬውም የብዙሃን ስፖርት መርሃ ግብር ለአዲስ አበባ አረንጓዴነት የድርሻዬን…

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና፣ ፋሲል ከነማ እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የ6ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ተደርገዋል። አዲስ አበባ ላይ ሃዲያ ሆሳዕናን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፏል። ቡናማዎቹ ጨዋታውን 5 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። በሌሎች ጨዋታዎች ደግሞ አዳማ ከተማ ከጅማ አባ ጅፋር እንዲሁም…

ጋና በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞችን አሰናበተች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋና እግር ኳስ ማህበር በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የብሄራዊ ቡድን የአሰልጣኝ አባላት ማሰናበቱን አስታወቀ። ማህበሩ የወንዶችና የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ እና ረዳቶቻቸውን ከስራ ማሰናበቱን አስታውቋል። ስንበቱ በሁለቱም ጾታዎች የታዳጊ፣ ወጣትና ዋናውን ቡድን አሰልጣኞችና ረዳቶቻቸውን ያካተተ ነው። ማህበሩ…

በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም የሚካሄደው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንደቀጠለ ነው

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም የሚካሄደው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንደቀጠለ ነው፡፡ በርካታ ታዳጊ አትሌቶች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከታህሳስ 20 2012 ዓ.ም ጀምሮ በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ እስካሁን በተደረጉ ውድድሮች በአሎሎ ውርወራ፣ በዲስከስስ…