ስፓርት
የ2017 ዓ.ም ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድርን አትሌት ብሬነሽ ደሴ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2017 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድርን አትሌት ብሬነሽ ደሴ 1ኛ በመውጣት ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡
በውድድሩ አትሌት አብዙ ከበደ 2ኛ እንዲሁም መቅደስ ሽመልስ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ተከታትለው ገብተዋል።
የ2017 ዓ.ም ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድርን በቀዳሚነት ያጠናቀቀችው አትሌት ብሬነሽ ደሴ 50 ሺህ ብር ሽልማት ይበረከትላታል።
በ22ኛ ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ ሩጫ ውድድር 16 ሺህ ተሳታፊዎች የተካፈሉ…
Read More...
የካራባኦ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የካራባኦ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ምሽት 1 ሠዓት ከ30 ላይ በዌምብሌይ ስታዲየም በሊቨርፑል እና ኒውካስል ዩናይትድ መካከል ይደረጋል፡፡
ሊቨርፑል በግማሽ ፍፃሜው የሰሜን ለንደኑን ክለብ ቶተንሀም ሆትስፐርን አሸንፎ ለፍፃሜ መብቃቱ ይወሳል፡፡
እንዲሁም ኒውካስል ዩናይትድ ሌላኛውን የሰሜን ለንደን ክለብ አርሰናልን አሸንፎ ነው…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከቼልሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ29ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር አርሰናል በሜዳው 10 ሠዓት ከ30 ላይ ከቼልሲ ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ ተጠባቂ ነው፡፡
በ55 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አርሰናል፤ ቼልሲን ለማሸነፍ እና ከተከታዮቹ ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማስፋት ወደ ሜዳ ይገባል።
በሁሉም ውድድር ባለፉት አራት ጨዋታዎች…
በናንጂንግ በሚካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና 14 ኢትዮጵያዊያን ይሳተፋሉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቻይና ናንጂንግ በሚካሄደው የዘንድሮው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ 14 አትሌቶች እንደሚሳተፉ ተገለጸ፡፡
የሁለት ጊዜ የሻምፒዮናው ባለክብር መለሰ ንብረት እና ሳሙኤል ተፈራ በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ኢትዮጵያ ይወክላሉ፡፡
በሪሁ አረጋዊ፣ ቢኒያም መሃሪ እና ጌትነት ዋለ በወንዶች 3 ሺህ ሜትር…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አምስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ29ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር ለቀጣይ ዓመት የአውሮፓ መድረክ ተሳትፎ ወሳኝነት ያላቸው ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
የቀጣይ ዓመት የቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎን ለማግኘት የሚያልሙት ማንቼስተር ሲቲዎች ምሽት 12 ሰዓት ላይ በኢቲሃድ ብራይተንን የሚያስተናግዱበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
በ47 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ…
ሮናልዶ ከፕሬዚዳንትነት ምርጫ እራሱን አገለለ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀድሞው የብራዚል እና ሪያል ማድሪድ አንጋፋ ተጫዋች ሮናልዶ ሉዊስ ናዛሪዮ ዲሊማ ከሀገሩ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነት ምርጫ እራሱን ማግለሉን ይፋ አደረገ፡፡
የ48 ዓመቱ የቀድሞ ዝነኛ ተጫዋች፤ የወቅቱን የብራዚል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኤድናልዶ ሮድሪጌዝ ለመተካት በሚደረገው ምርጫ በዕጩነት እንደሚቀርብ ይፋ…