Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የካፍ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ በካይሮ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ በግብጽ ካይሮ መካሄድ ጀምሯል፡፡ ከዋናው ጉባዔ አስቀድሞ የሚካሄደው የክፍለ አህጉር ማህበራት ስብሰባ በዛሬው ዕለት የካፍ ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞሴፔ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል። በነገው ዕለት የካፍ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ የሚከናወን ሲሆን÷የፊታችን ረቡዕ ደግሞ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት እና የካፍ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኢሳያስ ጅራ፣  ምክትል…
Read More...

ባሕር ዳር ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት1፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ22ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ባሕር ዳር ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የባሕር ዳር ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ፍቅረሚካኤል ዓለሙ በ90ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ ባሕር ዳር ከተማ በ33 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በሊጉ ሶስት ተከታታይ…

ቼልሲ ሌስተር ሲቲን በማሸነፍ ደረጃውን አሻሻለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ28ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቼልሲ በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ሌስተር ሲቲን አስተናግዶ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ለምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ ማርክ ኩኩሬላ በ60ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡ ባለ ሜዳው ቡድን ቼልሲ በመጀመሪያው አጋማሽ ፍፁም ቅጣት ምት አግኝተው…

በሊዝበን ግማሽ ማራቶን አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዛሬው ዕለት በፖርቹጋል ሊዝበን ከተማ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ አሸንፋለች፡፡ አትሌት ፅጌ ርቀቱን 1 ሰዓት 4 ደቂቃ ከ21 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነችው፡፡ ኬንያዊቷ አትሌት ሩዝ ቼፕንጌቲች 1 ሰዓት…

ማንቼስተር ዩናይትድ ከአርሰናል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ28ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው ኦልድትራፎርድ አርሰናልን ያስተናግዳል። ደካማ የውድድር ዓመት እያሳለፈ የሚገኘውና በሁሉም ውድድር ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ድል ማድረግ የተሳነው ማንቼስተር ዩናይትድ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ወደ ሜዳ ይገባል።…

ማንቼስተር ሲቲ በፕሪሚየር ሊጉ 9ኛ ሽንፈቱን አስተናገደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ28ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኖቲንግሃም ፎረስት ማንቼስተር ሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡ 9 ሠዓት ከ30 ላይ በተደረገው ጨዋታ፤ የኖቲንግሃም ፎረስትን ብቸኛ ጎል ካሉም ሁድሰን ኦዶይ አስቆጥሯል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም የአሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ ቡድን ኖቲንግሃም ፎረስት፤ ነጥቡን ወደ 51 ከፍ በማድረግ…

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሥድስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ28ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሥድስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በወጣው መርሐ-ግብር መሠረት 9 ሠዓት ከ30፤ ኖቲንግሃም ፎረስት በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም ማንቼስተር ሲቲን ያስተናግዳል፡፡ በውድድር ዓመቱ አስገራሚ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው የአሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ ቡድን ኖቲንግሃም ፎረስት፤…