Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ምሁራንን ሸለመ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለየዩ ዘርፎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ምሁራን ሽልማት ሰጠ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ሽልማቱን የሰጠው ለባህሩ ዘውዴ (ፕ/ር)፣ ጌትነት ታደለ (ፕ/ር) እንዲሁም በቀለ ጉተማ (ፕ/ር) ነው፡፡

በተጨማሪም ከአራት አስርት ዓመታት በላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን በትጋት ሲያገለግሉ ለቆዩት ለተሰማ ተአ (ፕ/ር)፣ ተስፋዬ ሺፈራው (ዶ/ር) እና ተ/ሐይማኖት ገ/ስላሴ (ዶ/ር) ሽልማት አበርክቷል።

ምሁራኑ በመማር ማስተማር፣ በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ ነው የሜዳሊያ ሽልማት የተበረከተላቸው።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.