Fana: At a Speed of Life!

የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ የተከናወኑ አበይት ተግባራትን እየገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ የተከናወኑ አበይት ተግባራትን በደብረብርሃን ከተማ እየገመገመ ነው፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ወረዳዎችና የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር በጋራ ምክክር እያካሄዱ ባለበት በዚህ መድረክ በአማራ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አህመዲን መሀመድ(ዶ/ር)ን ጨምሮ የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደርና የሰሜን ሸዋ ዞን አመራሮች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ እና የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ዋና ሰብሳቢ ሌተናል ጀነራል ሹማ አብደታ በወቅቱ እንዳሉት÷ የግምገማው ዓላማ ህዝቡን በፍጥነት ወደ ሰላሙ ለመመለስ የተከናወኑ እና ወደፊት መከናወን ስላለባቸው የልማትና የሰላም ስራዎች ላይ መወያየት ነው።

በመድረኩ የልማትና የሰላም አጀንዳዎችን አቀናጅቶ ከመምራት አኳያ ያጋጠሙ ፈተናዎችንና ጠንካራ ተግባራትን የሚፈተሹ እንደሆነም ተመላክቷል።

በታለ ማሞ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.