Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ልዩ አዳሪና ልዩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ፌስቲቫል መዝጊያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ልዩ አዳሪ እና ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፌስቲቫል መዝጊያ መርሃ ግብር ዛሬ ተካሂዷል።

ፌስቲቫሉ ፈጠራን ማበረታታት፣ የውድድር ስሜት መፍጠርና ተማሪዎችን በአንድ ማዕከል በማምጣት ልምድ እንዲቀያየሩ ማድረግን አላማ አድርጎ ላለፉት አራት ቀናት ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ተማሪዎቹ በትምህርት፣ በስፖርት እና በባህል ዘርፎች የተለያዩ ተግባራትን እና ውድድሮችን ተካሂደው አሸናፊ ለሆኑ ተማሪዎች፣ ቡድኖችና ትምህርት ቤቶች እውቅናና ሸልማት ተሰጥቷል።

ፌስቲቫሉ ትውልዱ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ የበለጠ እውቀቱ እንዲዳብር ከማድረግ ባለፈ የሳይንስና ሂሳብ እንዲሁም የፈጠራ ስራዎች ላይ በማተኮር ለሀገር እድገት ቁልፍ ሚና እንዲጫወት ያስቻለ ነው ተብሏል፡፡

ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተገኙ ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎች በተሳተፉበት በዚህ ፌስቲቫል የክልሉ ትምህርት ቢሮ አመራሮችና ከክልሉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ መምህራን ተሳተፈዋል።

ፌስቲቫሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ቶላ በሪሶና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት መከፈቱ የታወሳል።

በቅድስት ዘውዱ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.