Fana: At a Speed of Life!

የ”ሔር ኢሴ” በዩኔስኮ መመዝገብ የቱሪዝም እድገትን ለማፋጠን ፋይዳው የጎላ ነው-አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ”ሔር ኢሴ” በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ)መመዝገብ የቱሪዝም እድገትን ለማፋጠን የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

አቶ አደም ፋራህ የ”ሔር ኢሴ” ባህላዊ ህግ በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ የትምህርት እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ በመመዝገቡ የተሰማቸውን ደስታ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

“ሔር ኢሴ”ን በዩኔስኮ በማስመዝገብ ሂደት ሀገራቱ ያሳዩት የጋራ ጥረት ጎረቤት ሀገራት በጋራ ጉዳዮች ላይ በቁርጠኝነት ተባብረው ከሰሩ የሁሉንም ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስኬቶችን ማስመዝገብ እንደሚችሉ አይነተኛ ማሳያ ነው ሲሉም ነው የገለጹት ።

“ሔር ኢሴ” ማህበራዊ ትስስርን ለማጠናከር፣ የዜጎችን መብቶች ለማስጠበቅና አለመግባባቶች በምክክር ፍትሃዊ ውሳኔ እንዲያገኙ ለማድረግ የሚረዳ እንዲሁም ለመደበኛ የፍትህ ሥርዓትም አጋዥ የሆነ ባህላዊ ህግ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ለ”ሔር ኢሴ” የተሰጠው እውቅና ባህሉን በሚገባ ለመጠበቅ፣ ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍና የቱሪዝም እድገትን ለማፋጠን የሚኖረው ፋይዳ የጎላ እንደሆነም አንስተዋል፡፡

አቶ አደም ፋራህ ቅርሱን ጠብቀው ላቆዩ አባቶች እና በምዝገባ ሂደት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.