Fana: At a Speed of Life!

ትምህርት ሚኒስቴር ከጣሊያን ከፍተኛ ትምህርትና ምርምር ሚኒስቴር ጋራ ለመስራት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር እና የጣሊያን ከፍተኛ ትምህርትና ምርምር ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና የጣልያን ከፍተኛ ትምህርት እና ምርምር ሚኒስትር አና ማሪያ ፈርመውታል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዚሁ ወቅት÷ ስምምነቱ በትምህርይት ዘርፍ የተጀመሩ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።

በዘርፉ በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ እንዲሆኑ እየተሰራ ያለውን ሥራ እና በትምህርቱ ዘርፍ ትብብር የሚሹ ጉዳዮችን ለሚኒስትሯ አብራርተውላቸዋል።

አና ማሪያ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ የጣሊያን አጋር መሆኗን አንስተው ሀገራቱ በትምህርት ዘርፍ በላቀ ትብብር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ስምምነቱ በሀገራቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ቀጥተኛ ትብብር እንዲኖር የሚያግዝ መሆኑ መመላከቱን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.