Fana: At a Speed of Life!

በራስ አል ኬማህ  ግማሽ ማራቶን አትሌት እጅጋየሁ ታየ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች በተካሄደው የራስ አል ኬማህ የሴቶች ግማሽ ማራቶን አትሌት እጅጋየሁ ታየ ድል ቀንቷታል፡፡

እጅጋየሁ ግማሽ ማራቶኑን 1 ሰዓት ከአምስት ደቂቃ ከ52 ሴኮንድ በመጨረስ ነው ማሸነፍ የቻለችው፡፡

ኬኒያዊያኖቹ ጁዲ ኬምቦ እና ጀሲካ ቼላንጋት ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን ማጠናቀቃቸውን ከአዘጋጅ ኮሚቴው ድረ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ በወንዶች የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ገመቹ ዲዳ 59 ደቂቃ ከ25 ሴኮንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ ኬኒያዊው አሌክስ ማቴታ በ5 ሴኮንዶች ቀድሞ በመግባት ወድድሩን በቀዳሚነት አጠናቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.