Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ዘላቂ ሰላምን በማፅናት ልማትን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዘላቂ ሰላምን በማፅናት ልማትን ለማረጋገጥ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል፡፡

በክልሉ የአስተዳደር ጉዳዮች ክላስተር ስር የሚገኙ ተቋማት የግማሽ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ በባሕር ዳር ከተማ ተካሂዷል፡፡

በም/ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ ደሳለኝ ጣሰው በዚህ ወቅት÷የክልሉ ሰላም በማፅናት ልማትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህ ረገድም ልማትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ጠንካራ መሰረት እየተገነባ ይገኛል ነው ያሉት።

በየደረጃው ለሚገኘው የጸጥታ መዋቅር ሰፊና ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት እንዲሁም ህብረተሰቡ የጸጥታ ሃይሉ አጋዥ በመሆን እንዲሰራ መደረጉን አንስተዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስየ ደጀን በበኩላቸው÷ የክሉሉን ሰላም በዘላቂነት ማስጠበቅ የሚችል አስተማማኝ የፖሊስና የጸጥታ ሃይል መደራጀቱን አንስተዋል።

በዚህም በከተሞችም ይሁን በገጠር አካባቢ የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት የሚያውኩ ወንጀለኞች ላይ ርምጃ እየተወሰደና ለሕግ ተላልፈው እንዲሰጡ እየተደረገ ነው መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.