መድፈኞቹ ሌስተር ሲቲን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ወደ ኪንግ ፓወር ስታዲየም አቅንቶ ሌስተር ሲቲን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የመድፈኞቹን ሁለቱንም ግቦች ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው ስፔናዊው ሚኬል ሜሪኖ አስቆጥሯል፡፡
አርሰናል ድሉን ተከትሎ በደረጃ ሰንጠረዡ ከመሪው ሊቨርፑል ያለውን ልዩነት በ4 ነጥብ በማጥበብ በ53 ነጥብ 2ኛ ደረጃውን ማጠናከር ችሏል፡፡