Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ሩሲያ በጤና ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የጤና ሥርዓትን መደገፍና የደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታልን አሰራር ማዘመን የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል ።

የመግባቢያ ስምምነቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና የሩሲያ ጤና ሚኒስትር ሚክሄል ሙራሽኮ ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ የደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታልን አሰራርና አያያዝ በማዘመን የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

ሁለቱ ወገኖች የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎትን ማሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ዶ/ር መቅደስ ሩሲያ የደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታልን እና በኢትዮጵያ ያለውን የጤና ስርዓት ለመደገፍ በትብብር ለመስራት ያላትን ተነሳሽነት አድንቀው ÷ትብብሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ሚክሄል ሙራሽኮ በመገንባት ላይ የሚገኘውን የቅዱስ ጳውሎስ የጨረር ሕክምና ማዕከል የጎበኙ ሲሆን÷በዚህ ወቅትም ሩሲያ በኢትዮጵያ ለኒዩክሌር ሕክምና የሚሆን ግብዓት ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.