Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አጽዋማትን በማስመልከት የምግብ ፍጆታ ድጋፍ አደረገ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የረመዳን እና የዐብይ ጾምን ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የምግብ ፍጆታ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉን የከተማዋ ከንቲባ ከድር ጁሀር እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች አስረክበዋል፡፡

ለ550 የማህበረሰብ ክፍሎች የተደረገው ድጋፍ 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ ፍጆታ መሆኑን የከተማዋ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በቀጣይም 600 ለሚሆኑ የገጠር ነዋሪዎች መሰል ድጋፍ እንደሚደረግ የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር ተግባራት የአብሮነትንና የመደጋገፍ ባህልን ከማሳደግ አንጻር ትልቅ ሚና እንዳላቸውም በዚህ ወቅት ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.