ጂ አይ ዜድ ከኢትዮጵያ ጋር በግብርናው ዘርፍ ያለውን ትብብር እንደሚያጠክር ገለጸ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከጀርመን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር (ጂ አይ ዜድ) የግብርና ፕሮግራም ኃላፊ አንድሪያ ዊሊያም-ሰም ጋር ተወያይተዋል፡፡
ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፥ ጂ አይ ዜድ የአፈር ለምነትን ለመጠበቅ በተሰራው ስራ የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ጉልህ አስተዋጽዖ ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ የሚተገበሩ አዳዲስ ፕሮግራሞችን ለመተግበር ከጂ አይ ዜድ ጋር በትብብር እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡
አንድሪያ ዊሊያም-ሰም በበኩላቸው÷ ተቋማቸው ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በእርሻ ልማት፣ በአፈር ለምነትና በእንስሳት ዘርፍ በትብብር እየሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
አዳዲሶቹ ፕሮጀክቶች በቡና ልማት፣ በግብርና ሜካናይዜሽንና በእንስሳት ሀብት እንዲሁም በተፈጥሮ ሀብት ልማት ላይ ከግሉ ዘርፍ ጋር በትብብር እንደሚተገበሩ መጥቀሳቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።