የሴቶችን ጥቃት ለፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ መጠቀም ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ ተግባር ነው – ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሴቶችን ጥቃት ለፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ መጠቀም ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ ተግባር መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ሰሞኑን ብርቱካን ተመስገን ተብላ በምትጠራ ሴት ሀሰተኛ ታሪክ ላይ ተንተርሶ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚነሱ ሃሳቦችን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ፤ በሴቶች ላይ የሚፈጸምን ጥቃት ማውገዝና መቃወም ከሁሉም የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው ብለዋል።
ብርቱካን ተመስገን ተብላ በምትጠራ ሴት ሀሰተኛ ታሪክ ላይ ተንተርሶ የተለቀቀው መረጃ ግን በሴቶችና ህጻናት ላይ ያልተገባ መረጃን ለማህበረሰቡ ያደረሰ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ድርጊቱ ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ እና የሚወገዝ ተግባር መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
የሴቶችን ጥቃት ለመከላከል ተገቢውን ማስረጃ በማቅረብና መፍትሄ ሊያመጣ በሚችል መልኩ ብቻ ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
በሰለሞን በየነ