ቴሌ ብር በቀን 7 ቢሊየን ብር እያንቀሳቀሰ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቴሌ ብር ለኢትዮጵያ ዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ገለጹ፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ እንዳሉት÷ቴሌ ብር በደንበኞች ቁጥር ብዛትም ሆነ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ከፍተኛ እድገት እያስመዘገበ ነው፡፡
አሁን ላይ በቴሌ ብር በቀን 7 ቢሊየን ብር እንደሚንቀሳቀስ ጠቁመው÷ይህም ለዲጂታል ኦኮኖሚ ግንባታ ሚናው ጉልህ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ቴሌ ብር አዳዲስ መተግበሪያዎችን እና አሰራሮችን በመፍጠር ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ቴሌ ብር ቀልጣፋና አስተማማኝ አገልግሎት እንዲሰጥም ከሳይበር ደህንነት ጋር በተያያዘ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ነው የገለጹት፡፡
ኢትዮ-ቴሌኮም ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት እንዲሁም አካታችነት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አስገንዝበዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ