Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ከኤፍኤስዲ አፍሪካ ጋር በትብብር ለመስራት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ከአፍሪካ የፋይንናስ ማጠናከሪያ ኤጀንሲ (ኤፍኤስዲ አፍሪካ) ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት መፈራረሙን አስታውቋል፡፡

ተቋሙ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መግለጫ÷ ከኤፍኤስዲ አፍሪካ እና ኤፍኤስዲ ኢትዮጵያ ጋር የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ልማትን ለመደገፍ ያለመ ስምምነት መፈረሙን ገልጿል፡፡

በስምምነቱ መሰረትም ከተቋማቱ ጋር በግንዛቤ ፈጠራ፣ አዲስ የፋይናንስ ምንጮችን በማስተዋወቅ እንዲሁም በልምድ ልውውጥ ዘርፍ በትብብር እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡

ግልፅ፣ ተደራሽ እና አካታች የገበያ ስርዓትን ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን የገለፀው ተቋሙ÷ ይህም በኢትዮጵያ እየተሻሻለ በመጣው የፋይናንስ ስነ-ምህዳር ውስጥ እገዛ እንደሚያደርግ አስገንዝቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.