ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ25ኛው ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም 3:30 ላይ በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሳይመን ፒተር ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ሦስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
የሊጉ ጨዋታ ቀጥሎ ሲካሄድ ቀን 9 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡና ከባሕር ዳር ከተማ እንዲሁም ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሀዋሳ ከተማ ከወላይታ ድቻ ይገናኛሉ።
በሌላ ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ወላይታ ድቻን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ያሸነፈ ሲሆን÷የሀዋሳ ከተማን የማሸነፊያ ግብ አሊ ሱሌማን ከመረብ አሳርፏል፡፡