ኢትዮጵያና ቤላሩስ ወታደራዊ ትብብራቸውን ለማጠናከር መከሩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) ከቤላሩስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማክሲም ሪዚሄንኮቭ ጋር ተወያይተዋል፡፡፡
በውይይታቸውም ሀገራቱ በወታደራዊ እና ጸጥታ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ማስፋትና ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) በዚሁ ወቅት÷ ሁለቱ ሀገራት የጋራ እሴት፣ ታሪክና የባህል መመሳሰል ያላቸው መሆኑን አውስተዋል፡፡
ይህንን እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ የሁለትዮሽ ትብብሩን ይበልጥ ለማሳደግ ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል፡፡
ማክሲም ሪዚሄንኮቭ በበኩላቸው÷ ሁለቱ ሀገራት በወታደራዊ ስልጠና፣ በመከላከያ ቴክኖሎጂ ልውውጥና በመሳሰሉ መስኮች ያላቸውን ትብብር ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የሀገራቱን ሁለንተናዊ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውንም የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡