ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለቻይናውያን ባለሀብቶች ምቹ ናት – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለቻይናውያን ባለሀብቶች ምቹ መሆኗን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቻይና ሕዝብ የፖለቲካ ምክክር ጉባኤ ብሔራዊ ኮሚቴ ምክትል ሊቀ መንበር እና የቻይና የኢንዱስትሪና የንግድ ፌዴሬሽን ሊቀመንበር ጋኦ ዩንሎንግ እና የልዑክ ቡድናቸው ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት፣ የኢኮኖሚ ልማት እና የንግድ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ጋር መምከራቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።
ጋኦ ዩንሎንግ የኢትዮጵያን የልማት እንቅስቃሴ ማድነቃቸውን ገልጸው÷ በተለይም አዲስ አበባ በእጅጉ እንደተለወጠችና ባዩት ስኬታማ ሥራ እንደተደነቁ መናገራቸውን ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለቻይናውያን ባለሀብቶች ምቹ መሆኗን እና በሁኔታዎች የማይቀያየር የሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂካዊ አጋርነት በኢኮኖሚው መስክም ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተግባብተናል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡