ለኢትዮጵያ ፖሊስ ምስረታ በዓል ዝግጅት ኅብረተሰቡ ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፖሊስ የተመሰረተበት 116ኛ ዓመት ከሚያዝያ 19 እስከ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ ሁነቶች እንደሚከበር ተገልጿል።
የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ረዳት ኮሚሽነር ሞገስ ቸኮል በሰጡት መግለጫ÷ በሁነቱ የኢትዮጵያ ፖሊስ ታሪካዊ አመጣጥን እና የፖሊስ ያለፉት ዓመታት ሪፎርም ሥራዎች የሚዳስሱ ጽሑፎች እና ሲምፖዚዬም እንደሚካሄድ ተናግረዋል።
በመርሐ ግብሩ ሰባት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ፖሊስ አባላት ስፖርታዊ ውድድሮችን እንደሚያካሂዱ ነው የጠቀሱት፡፡
የውጭ ሀገራት የፖሊስ አመራሮች እና ተወካዮች የሚሳተፉበት የተለያዩ ወታደራዊ ትርዒቶችን ያካተተ ሁነት ሚያዝያ 26 በመስቀል አደባባይ በርካታ እንግዶች በተገኙበት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።
በዓሉን በተመለከተ በሚደረጉ ዝግጅቶች ኅብረተሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ ቀርቧል።
በይስማው አደራው