Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ከቻይና ሕዝብ የፖለቲካ ምክክር ጉባዔ ብሔራዊ ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበርና የቻይና የኢንዱስትሪና ንግድ ፌዴሬሽን ሊቀመንበር ጋኦ ዩንሎንግ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ኮሚሽነሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በመሰማራት ቻይናውያን ባለሃብቶች ቀዳሚ ናቸው፡፡

አሁን ላይ ከ3 ሺህ 500 በላይ ቻይናውያን 9 ነጥብ 5 ቢለየን ዶላር ፈሰስ በማድረግ በኢንቨስትመንት ዘርፍ መሰማራታቸውን ተናግረዋል፡፡

ይህም በኢትዮጵያና ቻይና መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት፣ የኢኮኖሚ ልማት እና የንግድ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ያስችላል ነው ያሉት፡፡

በመጪው ግንቦት 4 እና 5 ቀን 2017 ዓ.ም በሚደረገው የኢንቨስት ኢን ኢትዮጵያ ፎረም ላይ ቻይናውያን ባለሃብቶች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ጋኦ ዩንሎንግ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያን የልማት እንቅስቃሴ አድንቀው፤ በቻይና የሚገኙ ከ55 ሺህ በላይ የንግድ ማህበራት በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡

የቻይና መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የኢንቨስትመንት፣ የኢኮኖሚ ልማትና የንግድ ትብብር ይበልጥ ለማሳደግ ፍላጎት እንዳለው መናገራቸውንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.