Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ልዑክ ከእስያ የመሠረተ ልማት እና ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ በ2025 የአይ ኤም ኤፍ እና ዓለም ባንክ ስብሰባ ጎን ለጎን ከእስያ የመሠረተ ልማት እና ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዚዳንት ጂን ሊኩን ጋር ተወያየ፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ላደረጉት ጉብኝት አመሥግነው፤ በወቅቱ የኢትዮጵያን የተለያዩ ዘርፎች ለማገዝ እና የመሠረተ ልማት ዕቅዶችን ለመደገፍ ቁርጠኛ ነን ማለታቸውን አስታውሰዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሊኩን በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለውን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና የሪፎርም መርሐ-ግብሮች አድንቀዋል።

ለኢትዮጵያ ልማት ድጋፍ ለማድረግ እና ቀጣይነት ያለው የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ምርታማነትን ለማሳደግ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል፡፡

የባንኩን ድጋፍ በፍጥነት በማሰባሰብ ከትራንስፖርትና ተያያዥነት ያላቸው መሠረተ ልማቶችን በገንዘብ በመደገፍ በባንኩ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን አጋርነት ለማጠናከር ከስምምነት ደርሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.