Fana: At a Speed of Life!

በአቶ አህመድ ሺዴ የተመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የዕዳ አያያዝ ሂደት ዙሪያ ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የዕዳ አያያዝ ሂደት ዙሪያ ከEurobond Holders ጋር ተወያይቷል።

የ2025 የዓለም ባንክ እና የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም የፀደይ ስብሰባ ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከኢትዮጵያ Eurobond Holders ጋር ገንቢ ውይይት አድርጓል።

እ.ኤ.አ. በማርች 2025 ከኢትዮጵያ ኦፊሴላዊ አበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር በመርህ ደረጃ የተደረሰውን የተሳካ ስምምነት ተከትሎ በ G20 የጋራ ማዕቀፍ መሰረት የኢትዮጵያ የዕዳ አያያዝ ሂደት ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዷል።

ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በተመለከተ ያለውን አሁናዊ የሂደት ደረጃ ለንግድ አበዳሪዎቹ አስረድተዋል።

ሁለቱም ወገኖች የዕዳ አያያዝ ድርድሮችን በጊዜ እና በብቃት ለመጨረስ ቀጣይነት ያለው ምክክር ለማድረግ ተስማምተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.