በአማራ ክልል 42 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት 42 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል፡፡
የቢሮው ም/ሃላፊ አቶ የኔሰው መኮንን እንደገለጹት÷በዘጠኝ ወራት የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ12 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ብልጫ አለው፡፡
ፍትሃዊ የግብር ሥርዓትን ለማስፈንና የገቢ አቅምን በመለየት አሟጦ ለመጠቀም ቴክኖሎጂ መር የግብር አሰባሰብና አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋቱን ጠቅሰዋል፡፡
የግብር አሰባሰቡን ውጤታማነት ለማሳደግም ሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ ርምጃ መወሰዱን ነው የተናገሩት፡፡
በዚህም 1 ሺህ 27 ግብር ከፋዮች ላይ በተደረገ ምርመራ 675 ሚሊየን ብር የያዙ ከ2 ሺህ 300 በላይ ሕገ-ወጥ ደረሰኞች መያዛቸውን አመልክተዋል፡፡
በደሳለኝ ቢራራ