Fana: At a Speed of Life!

የዘውዲቱ ሆስፒታል እና የኩላሊት እጥበት አገልግሎት …

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

ሆስፒታሉ በኩላሊት እጥበት ክፍሉ በቋሚነት ለ30 ሰዎች የኩላሊት እጥበት አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነ የክፍሉ ባልደረባ ዶ/ር አማኑኤል ዘረያዕቆብ፤ ከቋሚ የኩላሊት እጥበት ታካሚዎች በተጨማሪ ከ50 እስከ 60 ለሚሆኑ ሰዎች የአጭር ጊዜ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ደግሞ የአጭር ጊዜ የእጥበት አገልግሎት እንደሚሰጥ አንስተው፤ አገልግሎት ከዓመት እስከ ዓመት ሳይቋረጥ እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።

ስምንት የኩላሊት እጥበት አገልግሎት መስጫ ማሽኖች ያሉት ሆስፒታሉ፤ ለአብዛኛው ታካሚ በቋሚነት በሳምንት ሶስት ጊዜ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።

የኩላሊት እጥበት ክፍሉ አስተባባሪ የወርቅውሃ ፈቃዱ በበኩላቸው ታካሚዎች በጥሩ ሁኔታ አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ከታካሚዎች ጋር ያለን ግንኙነት ከሃኪም እና ታካሚ ባለፈ የቤተሰብ አይነት ቅርርብ ነው ብለዋል።

በሆስፒታሉ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት እያገኙ ያሉ ታካሚዎች ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደተናገሩት፤ በሆስፒታሉ ከሚያገኙት የህክምና አገልግሎት በተጨማሪ ስለህመሙ በቂ ግንዛቤ አግኝተዋል።

በሆስፒታሉ እየተሰጠ የሚገኘው አገልግሎት በጣም ጥሩ እንደሆነም ገልጸዋል።

በዮናስ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.