ኢትዮጵያ በርካታ ልምዶችን የቀሰመችበት ጉባዔ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ2025 የአፍሪካ ኢኖቬሽን የትምህርት ጉባዔ ኢትዮጵያ በርካታ ልምዶችን መቅሰሟን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ለአብነትም በአፍ መፍቻ ቋንቋ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እና ትምህርትን የሚያግዙ ይዘቶችን እንዴት ማዘጋጀት እንደሚገባ ልምድ ካላቸው ኩባንያዎች ተሞክሮ መውሰድ መቻሉን በሚኒስቴሩ የአይ ሲ ቲ እና ዲጅታል ትምህርት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዘላለም አሰፋ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
የኮምፒውተር ሳይንስ በሀገራችን የሚሰጠው ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ ነው ያሉት ሥራ አስፈፃሚው፤ በሌሎች ሀገራት ግን ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እንደሚሰጥ እና ይህም ተማሪዎችን ውጤታማ እንሆኑ ማስቻሉን ተረድተናል ብለዋል፡፡
ይህንን ልምድ በመቅሰም ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ጥረት ይደረጋል ሲሉም ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በጉባዔው ከሌሎች ሀገራት እና ኩባንያዎች ሌሎች ልምዶችን መቅሰም መቻሉን አስረድተዋል፡፡
በትዕግስት አብረሃም