አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦሮሚያ ባንክ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሥልጠና እና የኮንቬንሽን ማዕከል በገላን ከተማ አስተዳደር ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ባንኩ የህንጻ ዲዛየን መረጣና የእዉቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡
የኦሮሚያ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተፈሪ መኮንን እንደተናገሩት÷ የስልጠና እና የኮንቬንሽን ማዕከሉ በገላን ከተማ አስተዳደር በ15 ሄክታር መሬት ላይ ይገነባል፡፡
ማዕከሉ ከልህቀት አገልግሎት በተጨማሪ የስፖርት ማዘዉተሪያ፣ የሕክምና፥ የመኝታና ሌሎች መሠል አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
ማዕከሉ ከባንኩ እና ከሌሎች ባንኮች ሠራተኞችና ባለሙያዎች በተጨማሪ በክልልና በሀገር ደረጃ የባንክ ባለ ሙያ የልህቀት ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግልም ነው በመርሃ ግብሩ ያብራሩት፡፡
በዲዛይን መረጣና የዕዉቅና አሰጣጥ መርሃ ግብሩ ላይ የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ገመቹ ዋቅቶላን ጨምሮ የባንኩ የቦርድ አመራሮች፣ የገላን ከተማ አስተዳደር ተወካዮችና ሌሎች እንግዶች መሳተፋቸውን ከኦ ቢ ኤን ሆርን አፍሪካ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!