አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ነገ የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ/ም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያስገነባውን አዲስ ህንፃ የሚያስመርቅ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የምረቃ መርሀ ግብሩ ተጀምሮ እስሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ፖሊስ ይፋ አደረገ።
• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ ፍል ውሀ
• ከሳንጆሴፍ መብራት ወደ አራምቤ ሆቴል ወይም አምባሳደር
• ከለገሀር መብራት ወደ ብሔራዊ ቴአትር
• ከሰንጋ ተራ ወደ ብሔራዊ ቴአትር
• ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቴአትር
• ከሜትሪዮሎጂ ወደ ፖስታ ቤት
• ከሀገር አስተዳደር ወይም ከኢሚግሬሽን ወደ ብሔራዊ ቴአትር
• ከሸራተን ሆቴል ወደ አምባሳደር
• ከንግድ ማተሚያ ወደ ፍልውሀ
የሚወስዱ መንገዶች ከጠዋቱ 2፡00 ሠዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ ሲሆን በፍል ውሀ ወይም በምረቃው ስነ ስርዓት በሚካሄድበት 360 ዲግሪ ክልል ውስጥ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ሁሉም አሽከርካሪ ተገንዝቦ አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አስተላልፏል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!