Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በከተማ ጥራት የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገቡ 15 ከተሞች ተሸለሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁለተኛው የከተሞች መሰረተልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም በሀገር አቀፍ ደረጃ በከተማ ጥራት የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ 15 ከተሞች የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ተሽከርካሪ ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡
ሽልማት የተበረከተላቸው ከተሞችም ደሴ፣ ደብረታቦር፣ ባህርዳር፣ ቢሾፍቱ፣ ነቀምቴ፣ ጂማ፣ ጅጅጋ፣ ሀዋሳ፣ ቡታጅራ፣ሆሳዕና፣ ሰመራ-ሎጊያ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ሀረር እና ድሬዳዋ ናቸው፡፡
በሽልማት መርሃ ግብሩ የተገኙት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፥ ሽልማቱ ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እንዲሆኑ እንዲሁም የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ እንዲያዳብሩ ያስችላል ብለዋል፡፡
የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ተሽከርካሪዎቹ ከ51 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገዙ መሆናቸውንም ሚንስትሯ ገልጸዋል፡፡
በጀማል አህመድ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version