Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሀገርን ደህንነት ማስጠበቅ የሚያስችል ዘመናዊ ባህር ሃይል መገንባት ያስፈልጋል – ኮሞዶር ዋላፃ ዋቻ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገርን ደህንነት ማስጠበቅ የሚያስችልና ከውስጥና ከውጭ የሚመጡ ችግሮችን የሚመክት ዘመናዊ ባህር ሃይል መገንባት ፣ ማደራጀትና ማሰልጠን አስፈላጊ መሆኑን የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሞዶር ዋላፃ ዋቻ ገለጹ፡፡
ኮሞዶሩ በባህር ዳር ተገኝተው የባህር ሃይል መሠረታዊ ባህረኞች በውሃ አካል ላይ የሚሰጡ ግዳጆችን ለመወጣት የሚያስችል የውሃ ዋና ሥልጠና ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት ፥ የውጭ ሃገራት የእጩ መኮንን ሥልጠናዎችን እና ደብረ ዘይት ባቦጋያ ትምህርት ቤት የውሃ ዋና እንዲሁም የመርከብ የተግባር ሥልጠናዎችን ማከናወን ተችሏል፡፡
ስልጠናው በመርከብ ላይ ሊደረጉ የሚገቡ የጥንቃቄ ፣ የአደጋ መከላከል ደንቦችና በውሃ አካል ላይ የሚሰጡ ግዳጆችን ሊያሳልጥ የሚችል ትምህርት በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም የኢትዮጵያን ባህር ሃይል በፍጥነት ለግዳጅ ዝግጁ ከማድረግ አንፃር ጠቀሜታው ስትራቴጂካዊ ሲሆን፥ በሀገራችን መከላከያ ሃይል ላይ ተጨማሪ የማድረግ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡
“የመሠረታዊ ባህረተኞች አስተባባሪ ሊውትናንት ቡሰሪ ቡልጉ እና መሠረታዊ ባህረኛ ሰልጣኞች በበኩላቸው፥ ቀጣይ ከሚሰጥ ግዳጅ አኳያ በዋናነት ፀረ-ሽብር፣ የባህር ላይ ውንብድና፣ የባህር ላይ ደህንነት የመከላከል እንዲሁም በአየርና በውሃ አካል ላይ የታገዘ ተልዕኮ የምንፈፅም በመሆኑ የሚሰጠንን ስልጠና በአግባቡ እንወጣዋለን “ ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version