Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የገንዝብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱላህ ሀመዶክ ጋር በዛሬው ዕለት ተወያዩ፡፡

የገንዝብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የሁለቱን ሀገራት ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር አድርገዋል፡፡

በተለይ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በኢኮኖሚ እና በልማት ላይ ያላቸውን ትብብር ማጠናከርና ማሻሻል በሚችሉበት ሁኔታዎች እንደተወያዩ ነው ሱና የዘገበው፡፡

Exit mobile version